ኤርምያስ 51:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የተገደሉት በከለዳውያን ምድር ይወድቃሉ፤ የቈሰሉትም በውጭ ይወድቃሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በባቢሎን ምድር ታርደው፣ በአደባባዮቿም እስከ ሞት ቈስለው ይወድቃሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮችዋ በከተሞቻቸው መንገዶች ላይ ቈስለው ይሞታሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በከለዳውያንም ምድር ተገድለው፥ በሜዳዋም ላይ ተወግተው ይወድቃሉ። |
ስለዚህ ጐበዛዝቷ በአደባባይዋ ላይ ይወድቃሉ፤ በዚያም ቀን ሰልፈኞች ሁሉ ይወድቃሉ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።
ሰይፍ በፈረሶቻቸውና በሰረገሎቻቸው ላይ፥ በመካከልዋም በተቀላቀሉ ሕዝብ ላይ አለ፤ እነርሱም እንደ ሴቶች ይሆናሉ፤ ሰይፍ በመዝገቦችዋ ላይ አለ፤ ይበተናሉም።
ባቢሎንም ወደ ሰማይ ብትወጣ፥ ቅፅሮችዋንም በኀይልዋ ብታጸና፥ ከእኔ ዘንድ አጥፊዎች ይመጡባታል፥ ይላል እግዚአብሔር።