La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኤርምያስ 42:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እና​ንተ የም​ት​ፈ​ሩት ሰይፍ በዚያ በግ​ብፅ ምድር ያገ​ኛ​ች​ኋል፤ ስለ እር​ሱም የም​ት​ደ​ነ​ግ​ጡ​በት ራብ በዚያ በግ​ብፅ ይደ​ር​ስ​ባ​ች​ኋል፤ በዚ​ያም ትሞ​ታ​ላ​ችሁ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የፈራችሁት ሰይፍ በዚያ ያገኛችኋል፤ የሠጋችሁበት ራብ እስከ ግብጽ ድረስ ተከትሏችሁ ይመጣል፤ በዚያም ትሞታላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ይደርስባችኋል፥ የሚያስደነግጣችሁም ራብ በዚያ በግብጽ ይከተላችኋል፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ያ የምትፈሩት ጦርነት ይደርስባችኋል፤ የምትፈሩትም ራብ ተከትሎአችሁ ይሄዳል፤ በዚያም በግብጽ ትሞታላችሁ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የምትፈሩት ሰይፍ በዚያ በግብጽ ምድር ያገኛችኋል፥ ስለ እርሱም የምትደነግጡበት ራብ በዚያ በግብጽ ይደርስባቸኋል፥ በዚያም ትሞታላችሁ።

Ver Capítulo



ኤርምያስ 42:16
13 Referencias Cruzadas  

በደለኞችን ክፉ ነገር ይከተላቸዋል፤ ጻድቃንን ግን መልካም ነገር ያገኛቸዋል።


“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


እስ​ማ​ኤል የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ በሀ​ገሩ ላይ የሾ​መ​ውን የአ​ኪ​ቃ​ምን ልጅ ጎዶ​ል​ያ​ስን ስለ ገደ​ለው ከለ​ዳ​ው​ያ​ንን ፈር​ተ​ዋ​ልና።


“እና​ንተ ግን በዚች ምድር አን​ቀ​መ​ጥም ብትሉ፥ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰሙ፥


እነሆ ለመ​ል​ካም ሳይ​ሆን ለክ​ፋት እተ​ጋ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ በግ​ብ​ፅም ምድር ያሉት የይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ ያል​ቃሉ።


ሰይ​ፍን ትፈ​ራ​ላ​ችሁ፤ እኔም ሰይ​ፍን አመ​ጣ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ለባሪያዎቼስ ለነቢያት ያዘዝኋቸው ቃሎቼና ሥርዓቴ በአባቶቻችሁ ላይ አልደረሱምን? እነርሱም ተመልሰው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር በመንገዳችንና በሥራችን መጠን ያደርግብን ዘንድ እንዳሰበ እንዲሁ አድርጎብናል አሉ።


እን​ዲሁ ብን​ተ​ወ​ውም ሁሉ ያም​ኑ​በ​ታል፤ የሮም ሰዎ​ችም መጥ​ተው ሀገ​ራ​ች​ን​ንና ወገ​ና​ች​ንን ይወ​ስ​ዱ​ብ​ናል።”


“ነገር ግን የአ​ም​ላ​ክ​ህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ባት​ሰማ፥ ዛሬም ያዘ​ዝ​ሁ​ህን ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን ሁሉ ባት​ጠ​ብቅ፥ ባታ​ደ​ር​ግም፥ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይመ​ጡ​ብ​ሃል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በክ​ሳት፥ በን​ዳ​ድም፥ በጥ​ብ​ሳ​ትም፥ በት​ኵ​ሳ​ትም፥ በድ​ር​ቅም፥ በዋ​ግም፥ በአ​ረ​ማ​ሞም ይመ​ታ​ሃል፤ እስ​ክ​ት​ጠ​ፋም ድረስ ያሳ​ድ​ዱ​ሃል።


የአ​ም​ላ​ክ​ህ​ንም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስላ​ል​ሰ​ማህ፥ ያዘ​ዘ​ህ​ንም ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን ስላ​ል​ጠ​በ​ቅህ፥ እስ​ክ​ት​ጠፋ ድረስ እነ​ዚህ መር​ገ​ሞች ሁሉ ይወ​ር​ዱ​ብ​ሃል፤ ያሳ​ድ​ዱ​ህ​ማል፤ ያገ​ኙ​ህ​ማል።