ኤርምያስ 23:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ እነሆ እያንዳንዱ ከባልንጀራው ዘንድ ቃሌን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስለዚህ ቃሌን እርስ በእርስ በመሰራረቅ ከእኔ እንደ ተቀበሉ አድርገው የሚናገሩትን ነቢያት እቃወማለሁ” ይላል እግዚአብሔር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ፥ እነሆ፥ አንዱ ከሌላው ዘንድ ቃሎቼን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል ጌታ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንዱ ከሌላው ቃልን በመስረቅ ‘ይህ የእግዚአብሔር ቃል ነው’ እያሉ የሚናገሩትን ነቢያት እጠላለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ፥ እነሆ፥ እያንዳንዱ ከባልንጀራው ዘንድ ቃሌን በሚሰርቁ ነቢያት ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር። |
እነሆ በሜዳ ላይ ባለው ድንጋያማ ሸለቆ የምትቀመጥ ሆይ! እኔ በአንተ ላይ ነኝ፤ እናንተም፦ የሚያስደነግጠን ወይም ወደ መኖሪያችን የሚገባ ማን ነው? የምትሉ ሆይ! እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፤
እነሆ ከምላሳቸው ትንቢትን አውጥተው፦ እርሱ የእግዚአብሔር ሸክም ነው በሚሉ ነቢያት ላይ ነኝ፤ ይላል እግዚአብሔር፤
“ስለዚህም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ይሁዳን ሁሉ አጠፋ ዘንድ፥ ፊቴን ለክፋት በላያችሁ አደርጋለሁ።
“ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እንደምጐበኛችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር።
“ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ እኔ ነፍሳትን እንደ ወፍ በምታጠምዱባት በመከዳችሁ ላይ ነኝ፤ ከክንዳችሁም ወስጄ እቀድዳታለሁ፤ እንደ ወፍም የምታጠምዱአቸውን ነፍሳት እለቅቃለሁ።
ስለዚህ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ከንቱ ነገርን ስለ ተናገራችሁ፥ ሐሰተኛ ራእይንም ስለ አያችሁ፥ ስለዚህ እነሆ እኔ በእናንተ ላይ ነኝ፥ ይላል እግዚአብሔር።
ፊቴንም በእነርሱ ላይ አጸናለሁ፤ ከእሳትም አይወጡም፤ እሳትም ይበላቸዋል፤ ፊቴንም በእነርሱ ላይ በአጸናሁ ጊዜ እኔ እግዚአብሔር እንደ ሆንሁ ታውቃላችሁ።
መቅደሴን ያረክስ ዘንድ፥ የቅዱሳኔንም ስም ያጐስቍል ዘንድ ዘሩን ለሞሎክ አገልግሎት ሰጥቶአልና እኔ በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አከብዳለሁ፤ ከሕዝቡም መካከል ለይች አጠፋዋለሁ።
ፊቴንም አከብድባችኋለሁ፤ በጠላቶቻችሁም ፊት ትወድቃላችሁ፤ የሚጠሏችሁም ያሸንፉአችኋል። ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።
ነገር ግን ይናገር ዘንድ ያላዘዝሁትን ቃል በስሜ የሚናገር ነቢይ፥ በሌላ አማልክት ስም የሚናገር ነቢይም፥ እርሱ ይገደል።
የእግዚአብሔር ቍጣ፥ ቅንአቱም በዚያ ሰው ላይ ይነድዳል እንጂ እግዚአብሔር ይቅርታ አያደርግለትም፤ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈው ርግማን ሁሉ በላዩ ይኖራል፤ እግዚአብሔርም ስሙን ከሰማይ በታች ይደመስሰዋል።