የእግዚአብሔር መልአክም አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ይስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፤ እግዚአብሔር ሥቃይሽን ሰምቶአልና።
ኢሳይያስ 7:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅንም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ዐማኑኤል ትለዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እግዚአብሔር ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም ‘ዐማኑኤል’ ብላ ትጠራዋለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፥ እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች። |
የእግዚአብሔር መልአክም አላት፥ “እነሆ፥ አንቺ ፀንሰሻል፤ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፤ ስሙንም ይስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፤ እግዚአብሔር ሥቃይሽን ሰምቶአልና።
ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል።
በአንተና በሴቲቱ መካከል፥ በዘርህና በዘርዋም መካከል ጠላትነትን አደርጋለሁ፤ እርሱ ራስህን ይቀጠቅጣል፤ አንተም ሰኰናውን ትነድፋለህ።”
ራሔልም፥ “እግዚአብሔር ከፍ ከፍ አደረገኝ፤ ብርቱ ትግልንም ከእኅቴ ጋር ታገልሁ፤ አሸነፍሁም፤ እኅቴንም መሰልኋት” አለች፤ ስሙንም ንፍታሌም ብላ ጠራችው።
አዳምም ዳግመኛ ሚስቱን ዐወቃት፤ ፀነሰችም፤ ወንድ ልጅንም ወለደች። ስሙንም ቃየል በገደለው በአቤል ፈንታ እግዚአብሔር ሌላ ዘር ተክቶልኛል ስትል ሴት አለችው።
በዚያም ቀን፦ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፤ “እነሆ፥ መሠዊያው ይሰነጠቃል፤ በውስጡም ያለው ስብ ይፈስሳል” ብሎ ምልክት ሰጠ።
ምክርን ብትመክሩም እግዚአብሔር ምክራችሁን ይለውጣል፤ የተናገራችሁትም ነገር አይሆንላችሁም። እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ከይሁዳ ወንድ ሰውን ሁሉ ያጠፋል፤ ኀያላኑንም ይጨርሳል፤ ሰፈሩም በሰፊው ምድርና በሀገሮቻቸው ሁሉ ይሞላል፤” እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።
ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኀያል አምላክ፥ የዘለዓለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል፤
በዘመኑም ይሁዳ ይድናል፤ እስራኤልም ተዘልሎ ይቀመጣል፤ ይህም ስም እግዚአብሔር በነቢያት ኢዮሴዴቅ ብሎ የጠራው ነው።
አንቺ ከዳተኛ ልጅ ሆይ! እስከ መቼ ትቅበዘበዣለሽ? እግዚአብሔር በምድር ላይ አዲስ ነገር ፈጥሮአልና ሰው ወደ ድኅነት ይመጣል።”
“ቃሌም በላያችሁ ለክፋት እንዲጸና ታውቁ ዘንድ በዚች ስፍራ በክፉ እንደምጐበኛችሁ ምልክታችሁ ይህ ነው፥” ይላል እግዚአብሔር።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
“እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፤ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ይሉታል፤” የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኖአል፤ ትርጓሜውም “እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነው፤” የሚል ነው።
መልአኩም መልሶ እንዲህ አላት፥ “መንፈስ ቅዱስ ያድርብሻል፤ የልዑል ኀይልም ይጋርድሻል፤ ከአንቺ የሚወለደውም ቅዱስ ነው፤ የልዑል እግዚአብሔር ልጅም ይባላል።
እነርሱም አባቶቻችን ናቸው፤ ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ ተወለደ፤ እርሱም ከሁሉ በላይ የሆነ ለዘለዓለም ቡሩክ አምላክ ነው፤ አሜን።
እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።
የመውለጃዋም ወራት በደረሰ ጊዜ ሐና ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርስዋም፥ “ከሠራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር ለምኜዋለሁ” ስትል ስሙን “ሳሙኤል” ብላ ጠራችው።
እርስዋም የእግዚአብሔር ታቦት ስለ ተማረከች፥ ስለ አማቷና ስለ ባልዋም፦ የሕፃኑን ስም ዊቦርኮኢቦት ብላ ጠራችው።