ኢሳይያስ 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር እንዲህ አለ፥ “የጽዮን ቆነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውን እያሰገጉ በዐይናቸውም እያጣቀሱ፥ በእግራቸውም እያረገዱ፥ ልብሳቸውንም እየጐተቱ፥ በእግራቸውም እያማቱ ይሄዳሉና፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፣ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ኲራት አብዝተዋል፤ አንገታቸውን አስረዝመው በዐይናቸው ይጠቅሳሉ፤ አረማመዳቸውን ለውጠው የእግራቸውን አልቦ እያቃጨሉ በቀስታ ይራመዳሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኮርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉና |
እናንት የጽዮን ቈነጃጅት፥ እናቱ በሠርጉ ቀን በልቡ ደስታ ቀን ያቀዳጀችውን አክሊል ደፍቶ ንጉሥ ሰሎሞንን ታዩ ዘንድ ውጡ።
እነሆ፥ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ከኢየሩሳሌምና ከይሁዳ ኀይለኛውን ወንድና ኀይለኛዋን ሴት፥ የእንጃራን ኀይል ሁሉ፥ የውኃውንም ኀይል ሁሉ ያስወግዳል፤
እግዚአብሔር የጽዮንን ሴቶች ልጆችና ወንዶች ልጆች እድፍ ያጥባልና፥ በፍርድ መንፈስና በሚያቃጥል መንፈስም ከመካከላቸው ደምን ያነጻልና።
በዚያን ጊዜ እየታበዩ የሚፎክሩትን ከመካከልሽ አወጣለሁና፥ አንቺም በቅዱስ ተራራዬ ዳግመኛ አትኰሪምና በዚያ ቀን በእኔ ላይ ተላልፈሽ በሠራሽው ሥራ ሁሉ አታፍሪም።
ጌታችን ኢየሱስም መለስ ብሎ እንዲህ አላቸው፥ “እናንተ የኢየሩሳሌም ልጆች ሆይ፥ ለራሳችሁና ለልጆቻችሁ አልቅሱ እንጂ ለእኔስ አታልቅሱልኝ።