| ኢሳይያስ 3:16 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የኢየሩሳሌም ሴቶች ኲራት አብዝተዋል፤ አንገታቸውን አስረዝመው በዐይናቸው ይጠቅሳሉ፤ አረማመዳቸውን ለውጠው የእግራቸውን አልቦ እያቃጨሉ በቀስታ ይራመዳሉ።Ver Capítulo አዲሱ መደበኛ ትርጒም16 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፣ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፣ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ጌታ እንዲህ ይላል፤ የጽዮን ሴቶች ኰርተዋል፤ ዐንገታቸውን እያሰገጉ፤ በዐይናቸውም እየጠቀሱ ይሄዳሉ፤ እየተቈነኑ በመራመድ፤ የእግራቸውን ዐልቦ ያቃጭላሉ።Ver Capítulo የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 እግዚአብሔር እንዲህ አለ፥ “የጽዮን ቆነጃጅት ኰርተዋልና፥ አንገታቸውን እያሰገጉ በዐይናቸውም እያጣቀሱ፥ በእግራቸውም እያረገዱ፥ ልብሳቸውንም እየጐተቱ፥ በእግራቸውም እያማቱ ይሄዳሉና፤Ver Capítulo መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ደግሞም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ የጽዮን ቈነጃጅት ኮርተዋልና፥ አንገታቸውንም እያሰገጉ በዓይናቸውም እያጣቀሱ፥ ፈንጠርም እያሉ፥ በእግራቸውም እያቃጨሉ ይሄዳሉናVer Capítulo | 
በዚያን ቀን ጌታ የኢየሩሳሌምን ሴቶች ጌጣጌጥ ማለት የእግራቸውን አልቦ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ የአንገታቸውን ጌጣጌጥ፥ የጆሮአቸውን ጒትቻ፥ አምባራቸውን፥ የፊታቸውን መሸፈኛ፥ የጠጒራቸውን መሸፈኛ፥ በክንዳቸው ላይ የሚያደርጉትን ጌጥ፥ በወገባቸው ላይ የሚያስሩትን መቀነት፥ የሽቶ ጠርሙሳቸውን፥ ጥንቈላ የተጻፈበትን አሸንክታብ፥ የጣታቸውንና የአፍንጫቸውን ቀለበት፥ ለዓመት በዓል የሚሆነውን የክት ልብስ፥ መጐናጸፊያቸውንና ካባቸውን፥ የእጅ ቦርሳቸውን፥ መስታዋታቸውን፥ ከሐር የተሠራ የውስጥ ልብሳቸውን፥ ራስ ማሰሪያቸውንና ዐይነ ርግባቸውን ሁሉ ያስወግዳል።