La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 19:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ግብ​ፃ​ው​ያ​ን​ንም በጨ​ካኝ ጌቶች እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ጨካ​ኞች ነገ​ሥ​ታ​ትም ይገ​ዟ​ቸ​ዋል” ይላል የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ግብጻውያንን አሳልፌ ለጨካኝ ጌታ ክንድ እሰጣቸዋለሁ፤ አስፈሪ ንጉሥም ይገዛቸዋል” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ግብጻውያንንም ለጨካኝ ገዢዎች አሳልፌ እሰጣለሁ፤ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል፥ ይላል ልዑል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እነርሱን በጭካኔ ለሚገዛቸው ንጉሥ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እኔ ጌታ የሠራዊት አምላክ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ግብጻውያንንም በጨካኝ ጌታ እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ጨካኝ ንጉሥም ይገዛቸዋል ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 19:4
9 Referencias Cruzadas  

አስ​ተ​ም​ር​ሃ​ለሁ፥ በም​ት​ሄ​ድ​ባ​ትም በዚች መን​ገድ አጸ​ና​ሃ​ለሁ። ዐይ​ኖ​ቼን በአ​ንተ ላይ አጸ​ና​ለሁ።


“ግብ​ፃ​ው​ያን በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ይነ​ሣሉ፤ ወን​ድ​ምም ወን​ድ​ሙን፥ ሰውም ባል​ን​ጀ​ራ​ውን ይገ​ድ​ላል፤ ከተ​ማም ከተ​ማን፥ መን​ግ​ሥ​ትም መን​ግ​ሥ​ትን ይወ​ጋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለ፥ “ባሪ​ያዬ ኢሳ​ይ​ያስ ሦስት ዓመት ራቁ​ቱን በባዶ እግሩ እንደ ሄደ፥ እን​ዲሁ በግ​ብ​ፅና በኢ​ት​ዮ​ጵያ ላይ ሦስት ዓመት ምል​ክ​ትና ተአ​ም​ራት ይደ​ረ​ጋል።


እን​ዲሁ የአ​ሦር ንጉሥ የግ​ብ​ፅ​ንና የኢ​ት​ዮ​ጵ​ያን ምርኮ፥ ጐበ​ዛ​ዝ​ቱ​ንና ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቹን ራቁ​ታ​ቸ​ው​ንና ባዶ እግ​ራ​ቸ​ውን አድ​ርጎ፥ ገላ​ቸ​ው​ንም ገልጦ ለግ​ብፅ ኀፍ​ረት ይነ​ዳ​ቸ​ዋል።


ነፍ​ሳ​ቸ​ው​ንም በሚ​ፈ​ልጉ ሰዎች እጅ፥ በባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እጅ፥ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ቹም እጅ አሳ​ልፌ እሰ​ጣ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ ከዚ​ያም በኋላ እንደ ቀድ​ሞው ዘመን የሰው መኖ​ሪያ ትሆ​ና​ለች፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።”


ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እነሆ የግ​ብ​ፅን ምድር ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር እሰ​ጠ​ዋ​ለሁ፤ ብዛ​ቷ​ንም ይወ​ስ​ዳል፤ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ብዝ​በ​ዛ​ዋ​ንም ይበ​ዘ​ብ​ዛል፤ ይህም ለሠ​ራ​ዊቱ ደመ​ወዝ ይሆ​ናል።


ወን​ዞ​ች​ንም ምድረ በዳ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም በክፉ ሰዎች እጅ እሰ​ጣ​ለሁ፥ ምድ​ሪ​ቱ​ንና ሞላ​ዋ​ንም በባ​ዕ​ዳን እጅ ባድማ አደ​ር​ጋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሬ​አ​ለሁ።


እርስዋ ግን ተማርካ ፈለሰች፣ ሕፃናቶችዋ በመንገድ ሁሉ ራስ ላይ ተፈጠፈጡ፣ በከበርቴዎችዋም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፥ ታላላቆችዋም ሁሉ በሰንሰለት ታሰሩ።


ለሳ​ኦ​ልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነ​ገ​ረው፤ ሳኦ​ልም፥ “መዝ​ጊ​ያና መወ​ር​ወ​ሪያ ወዳ​ለ​ባት ከተማ ገብቶ ተገ​ኝ​ቶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእጄ አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​ታል” አለ።