La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢሳይያስ 16:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሞዓብ ዋይ በሉ፤ ሁሉም በሞ​ዓብ ዋይ ይላ​ሉና፤ በዴ​ሴት የሚ​ኖ​ሩም አያ​መ​ል​ጡም፤ ጠብን ያጭ​ራሉ፤ ያፍ​ራ​ሉም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ሞዓባውያን ዋይ ይላሉ፤ በአንድነትም ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት ከተማ ሰዎች ትዝታ፣ በሐዘን ያለቅሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይታ ያሰማ፤ ሁሉም ዋይታ ያሰማሉ፤ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህ ሞአብ ታልቅስ፤ ሰዎችም ሁሉ ስለ ሞአብ ያልቅሱ፤ በቂርሔሬስ ከተማ የነበረው ምርጥ ምግብ ትዝ እያላቸው በታላቅ ሐዘን ያለቅሳሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህ ሞዓብ ስለ ሞዓብ ዋይ ይላል፥ ሁሉም ዋይ ይላል፥ ስለ ቂርሐራሴት መሠራት በጥልቅ ኀዘን ታለቅሳላችሁ።

Ver Capítulo



ኢሳይያስ 16:7
8 Referencias Cruzadas  

ከተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም አፈ​ረሱ፤ በመ​ል​ካ​ሞ​ቹም እር​ሻ​ዎ​ቻ​ቸው ሁሉ ላይ እስ​ኪ​ሞሉ ድረስ እያ​ን​ዳ​ንዱ ሰው አንድ አንድ ድን​ጋይ ይጥል ነበር፤ የው​ኃ​ው​ንም ምን​ጮች ሁሉ ደፈኑ፤ የከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ው​ንም ቅጥር አፈ​ረሱ፤ የሚ​ያ​ም​ሩ​ትን ዛፎች ሁሉ ቈረጡ፤ ባለ ወን​ጭ​ፎ​ችም ከብ​በው መቱ​አ​ቸው።


ደግ​ሞም በእ​ስ​ራ​ኤል ዘንድ ደስታ ሆኖ​አ​ልና እስከ ይሳ​ኮ​ርና እስከ ዛብ​ሎን እስከ ንፍ​ታ​ሌ​ምም ድረስ ለእ​ርሱ አቅ​ራ​ቢያ የነ​በሩ በአ​ህ​ያና በግ​መል በበ​ቅ​ሎና በበሬ ላይ እን​ጀ​ራና ዱቄት የበ​ለስ ጥፍ​ጥ​ፍና የዘ​ቢብ ዘለላ የወ​ይ​ንም ጠጅ፥ ዘይ​ትም በሬ​ዎ​ች​ንና በጎ​ች​ንም፥ ፍየ​ሎ​ች​ንም በብዙ አድ​ር​ገው ያመጡ ነበር።


ለእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ለወ​ን​ዱም ለሴ​ቱም ለእ​ያ​ን​ዳ​ንዱ አን​ዳ​ንድ እን​ጀራ፥ አን​ዳ​ን​ድም ቍራጭ ሥጋ፥ አን​ዳ​ን​ድም የዘ​ቢብ ጥፍ​ጥፍ አካ​ፈለ።


ስለ​ዚህ ልቤ ስለ ሞዓብ እንደ መሰ​ንቆ ትጮ​ኻ​ለች። አጥ​ን​ቶ​ችም እንደ ተመ​ረገ ግድ​ግዳ ይሆ​ናሉ።


እነ​ር​ሱም፥ “ድም​ፃ​ቸ​ውን ዝቅ አድ​ር​ገው የሚ​ና​ገ​ሩ​ትን መና​ፍ​ስት ጠሪ​ዎ​ች​ንና ጠን​ቋ​ዮ​ችን ጠይቁ” ባሉ​አ​ችሁ ጊዜ፥ ሕዝቡ ከአ​ም​ላኩ መጠ​የቅ አይ​ገ​ባ​ው​ምን? ወይስ ለሕ​ያ​ዋን ሲሉ ሙታ​ንን ይጠ​ይ​ቃ​ሉን?


“ሞአብ ፈር​ሳ​ለ​ችና አፈ​ረች፤ አል​ቅሱ፥ ጩኹም፤ ሞአብ እንደ ጠፋች በአ​ር​ኖን አውሩ።


ሰለ​ዚህ ለሞ​አብ አለ​ቅ​ሳ​ለሁ፤ ለሞ​አ​ብም ሁሉ እጮ​ኻ​ለሁ፤ ለቂ​ር​ሔ​ሬስ ሰዎች አለ​ቅ​ሳ​ለሁ።