La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐጌ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፣ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ሰው የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፣ ያም ዕጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይም ሌላ ምግብ ቢነካ የተቀደሰ ይሆናልን?’ ” ካህናቱም፣ “የተቀደሰ አይሆንም” ብለው መለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፥ ዕጥፋቱ እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውንም መብል ቢነካ ያ የተነካው የተቀደሰ ይሆናልን? ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፥ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ።

Ver Capítulo



ሐጌ 2:12
8 Referencias Cruzadas  

ሰባት ቀን መሠ​ዊ​ያ​ውን ታነ​ጻ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ መሠ​ዊ​ያ​ውም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ይሆ​ናል፤ መሠ​ዊ​ያ​ው​ንም የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል።


የሞቱ ዝን​ቦች የተ​ቀ​መ​መ​ውን የዘ​ይት ሽቱ ያገ​ሙ​ታል፤ በስ​ን​ፍ​ናም ካለ ታላቅ ክብር ይልቅ ትንሽ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች።


ወደ ውጭ​ውም አደ​ባ​ባይ ወደ ሕዝብ በወጡ ጊዜ ያገ​ለ​ገ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ያው​ልቁ፤ በተ​ቀ​ደ​ሰ​ውም ዕቃ ቤት ውስጥ ያኑ​ሩት፤ ሕዝ​ቡ​ንም በል​ብ​ሳ​ቸው እን​ዳ​ይ​ቀ​ድሱ ሌላ​ውን ልብስ ይል​በሱ።


ሥጋ​ውን የሚ​ነካ ሁሉ ቅዱስ ይሆ​ናል፤ ማና​ቸ​ውም ልብስ ደም ቢረ​ጭ​በት የተ​ረ​ጨ​በ​ትን በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ያጥ​ቡ​ታል።


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ከእ​ርሱ ይበ​ላል፤ እር​ሱም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


ከካ​ህ​ናት ወገን የሆነ ወንድ ሁሉ ይበ​ላ​ዋል፤ በተ​ቀ​ደሰ ስፍ​ራም ይበ​ሉ​ታል፤ ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነው።


እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? መባው ነውን? ወይስ መባውን የሚቀድሰው መሠዊያው?


ፍር​ድ​ህን ለያ​ዕ​ቆብ፥ ሕግ​ህ​ንም ለእ​ስ​ራ​ኤል ያስ​ተ​ም​ራሉ፤ በማ​ዕ​ጠ​ን​ትህ ዕጣ​ንን፥ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ህም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሁል​ጊዜ ያቀ​ር​ባሉ።