ሐጌ 2:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፥ ዕጥፋቱ እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውንም መብል ቢነካ ያ የተነካው የተቀደሰ ይሆናልን? ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 አንድ ሰው የተቀደሰውን ሥጋ በልብሱ ዕጥፋት ቢይዝ፣ ያም ዕጥፋት እንጀራ ወይም ወጥ፣ የወይን ጠጅ ወይም ዘይት ወይም ሌላ ምግብ ቢነካ የተቀደሰ ይሆናልን?’ ” ካህናቱም፣ “የተቀደሰ አይሆንም” ብለው መለሱ። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 ለምሳሌ አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ ከመሠዊያ ላይ ወስዶ በመጐናጸፊያው ጠቅልሎ ቢይዝ፥ ልብሱም እንጀራና ወጥ፥ የወይን ጠጅና ዘይት ወይም ማናቸውንም ዐይነት ምግብ ቢነካ፥ ምግቡ ሁሉ በዚያ ሰው ምክንያት የተቀደሰ ሊሆን ይችላልን?” በላቸው፤ በዚህ መሠረት ነቢዩ ከጠየቃቸው በኋላ፥ ካህናቱ “የተቀደሰ ሊሆን አይችልም” ሲሉ መለሱ። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፣ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 አንድ ሰው የተቀደሰ ሥጋ በልብሱ ዘርፍ ቢይዝ፥ በዘርፉም እንጀራ ወይም ወጥ፥ ወይም የወይን ጠጅ፥ ወይም ዘይት፥ ወይም ማናቸውም መብል ቢነካ ያ የተነካው በውኑ ይቀደሳልን? ብለህ ካህናቱን ጠይቃቸው፥ ካህናቱም፦ አይሆንም ብለው መለሱ። Ver Capítulo |