በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
ዘፍጥረት 50:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አርባ ቀንም ፈጸሙለት፤ ሽቱ የሚቀቡበትን ቀን እንዲሁ ይቈጥራሉና፤ የግብፅም ሰዎች ሰባ ቀን አለቀሱለት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሬሳው እንዳይፈርስ መድኀኒት መቀባቱ በአገሩ ልማድ መሠረት አርባ ቀን ወሰደባቸው፤ ግብጻውያንም ሰባ ቀን አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መድኃኒት ቀማሚዎቹም በሀገሩ ልማድ መሠረት ሬሳውን ለማድረቅ አርባ ቀን ፈጀባቸው። ግብጻውያን ሰባ ቀን ሙሉ አለቀሱለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መድኃኒት ቀማሚዎቹም በሀገሩ ልማድ መሠረት ሬሳውን ለማድረቅ አርባ ቀን ፈጀባቸው። ግብጻውያን ሰባ ቀን ሙሉ አለቀሱለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አርባ ቀንም ፈጸሙለት የሽቱ መደረጊያው ወራት እንደዚሁ ይፈጸማልን የግብፅም ሰዎች ሰባ ቅን አለቀሱለት። |
በዮርዳኖስ ማዶ ወዳለችው ወደ አጣድ አውድማ ደረሱ፤ እጅግ ታላቅ በሆነ በጽኑ ልቅሶም አለቀሱለት፤ ለአባቱም ሰባት ቀን ልቅሶ አደረገለት።
የልቅሶውም ወራት ከተፈጸመ በኋላ ዮሴፍ ለፈርዖን መኳንንት እንዲህ ብሎ ተናገረ፥ “እኔ በፊታችሁ ሞገስን አግኝቼ እንደ ሆንሁ ለፈርዖን እንዲህ ብላችሁ ስለ እኔ ንገሩት፦
የተማረከችበትንም ልብስ ታወልቅላታለህ፤ በቤትህም ታስቀምጣታለህ፤ ስለ አባቷና ስለ እናቷ አንድ ወር ሙሉ ታለቅሳለች፤ ከዚያም በኋላ ትደርስባታለህ፤ ባልም ትሆናታለህ፤ እርስዋም ሚስት ትሆንልሃለች።
የእስራኤልም ልጆች በዮርዳኖስ በኢያሪኮ አቅራቢያ በሞዓብ ሜዳ ሠላሳ ቀን ለሙሴ አለቀሱለት፤ ለሙሴም ያለቀሱለት የልቅሶው ወራት ተፈጸመ።