La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 49:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“ስም​ዖ​ንና ሌዊ ወን​ድ​ማ​ማ​ቾች ናቸው፤ በጭ​ቅ​ጭ​ቃ​ቸ​ውና በጦ​ራ​ቸው ዐመ​ፅን ፈጸ​ሙ​አት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች፣ ሰይፎቻቸው የዐመፅ መሣሪያዎች ናቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው፥ ሰይፎቻቸው የዓመፃ መሣሪያ ናቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“ስምዖንና ሌዊ ወንድማማቾች ናቸው፤ ዐመፅ ለመፈጸም የጦር መሣሪያቸውን ያነሣሉ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስምዖንና ሌዊ ወንድማማች ናቸው ሰይፎቻቸው የዓመፅ መሣሪያ ናቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 49:5
8 Referencias Cruzadas  

በሥራው ራሱን የማያድን፥ ራሱን ለሚያጠፋ ወንድም ነው።


ከብ​ን​ያ​ምም ድን​በር ቀጥሎ ከም​ሥ​ራቅ ጀምሮ እስከ ምዕ​ራብ ድረስ ለስ​ም​ዖን አንድ የዕጣ ክፍል ይሆ​ናል።


ከስ​ም​ዖን ልጆች ነገድ የዓ​ሚ​ሁድ ልጅ ሰላ​ም​ያል፥


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እነ​ዚ​ህን ከተ​ሞ​ችና መሰ​ማ​ሪ​ያ​ቸ​ውን ለሌ​ዋ​ው​ያን በዕጣ ሰጡ።


ከስምዖን ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከሌዊ ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥ ከይሳኮር ነገድ ዐሥራ ሁለት ሺህ፥