La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 49:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እነ​ዚ​ህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ናቸው፤ አባ​ታ​ቸ​ውም ይህን ነገር ነገ​ራ​ቸው፤ ባረ​ካ​ቸ​ውም፤ እያ​ን​ዳ​ን​ዳ​ቸ​ው​ንም እንደ በረ​ከ​ታ​ቸው ባረ​ካ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እነዚህ ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው። ይህም እያንዳንዳቸውን ተገቢ በሆነው በረከት አባታቸው ሲባርካቸው የተናገረው ቃል ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እነዚህም ሁሉ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፥ አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም፥ እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንግዲህ እነዚህ ዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው፤ አባታቸው በባረካቸው ጊዜ ለእያንዳንዱ ተስማሚ የሆነውን የበረከት ቃል የተናገረው በዚህ ሁኔታ ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እነዚህም ሁሉ አሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ናቸው አባታቸው የነገራቸው ይህ ነው፥ ባረካቸውም እያንዳንዳቸውን እንደ በረከታቸው ባረካቸው።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 49:28
16 Referencias Cruzadas  

የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፤


“ብን​ያም ነጣቂ ተኵላ ነው፤ በጥ​ዋት ይበ​ላል፤ የማ​ረ​ከ​ው​ንም ምግ​ቡን በማታ ለሕ​ዝብ ይሰ​ጣል።”


እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እኔ ወደ ወገ​ኖች እሰ​በ​ሰ​ባ​ለሁ፤ በኬ​ጢ​ያ​ዊው በኤ​ፍ​ሮን እርሻ ላይ ባለ​ችው ዋሻ ከአ​ባ​ቶች ጋር ቅበ​ሩኝ፤ እር​ስ​ዋም በከ​ነ​ዓን ምድር በመ​ምሬ ፊት ያለች፥


ኤል​ያ​ስም፦ ስምህ እስ​ራ​ኤል ይሆ​ናል የሚል የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል እንደ ደረ​ሰ​ለት እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ነገድ ቍጥር ዐሥራ ሁለት ድን​ጋ​ዮ​ችን ወሰደ።


የዕ​ን​ቍም ድን​ጋ​ዮች እንደ እስ​ራ​ኤል ልጆች ስሞች ዐሥራ ሁለት ይሆ​ናሉ፤ በየ​ስ​ማ​ቸ​ውም ማኅ​ተም አቀ​ራ​ረጽ ይቀ​ረጹ፤ ስለ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ችም ይሁኑ።


እነሆ፥ ሕዝቡ እንደ አን​በሳ ደቦል ያገ​ሣል፤ እንደ አን​በ​ሳም ይነ​ሣል፤ ያደ​ነ​ውን እስ​ኪ​በላ፥ የገ​ደ​ለ​ው​ንም ደሙን እስ​ኪ​ጠጣ አይ​ተ​ኛም።”


ንጉሥ አግ​ሪጳ ሆይ፥ ዐሥራ ሁለቱ ነገ​ዶ​ቻ​ችን በመ​ዓ​ል​ትም በሌ​ሊ​ትም እር​ሱን እያ​ገ​ለ​ገሉ ወደ እር​ስዋ ይደ​ርሱ ዘንድ ተስፋ ያደ​ር​ጋሉ፤ አይ​ሁ​ድም የሚ​ከ​ስ​ሱኝ ስለ​ዚህ ተስፋ ነው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰው ሙሴ ሳይ​ሞት የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች የባ​ረ​ከ​ባት በረ​ከት ይህች ናት።


የእግዚአብሔርና የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሪያ ያዕቆብ ለተበተኑ ለዐሥራ ሁለቱ ወገኖች፤ ሰላም ለእናንተ ይሁን።


የታተሙትንም ቍጥር ሰማሁ፤ ከእስራኤል ልጆች ነገድ ሁሉ የታተሙት መቶ አርባ አራት ሺህ ነበሩ።