ዘፍጥረት 47:28 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም በግብፅ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ፤ የያዕቆብም መላው የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆነ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብ በግብጽ ዐሥራ ሰባት ዓመት ኖረ፤ ዕድሜውም አንድ መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም በግብጽ ምድር ዐሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ፥ የያዕቆብም የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብ ዐሥራ ሰባት ዓመት በግብጽ አገር ኖረ፤ ዕድሜውም መቶ አርባ ሰባት ዓመት ሆኖት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም በግብፅ ምድር አሥራ ሰባት ዓመት ተቀመጠ የያዕቆብም ሙላው የሕይወቱ ዘመን መቶ አርባ ሰባት ዓመት ነው። |
የያዕቆብም ትውልድ እንዲህ ነው። ዮሴፍ ዐሥራ ሰባት ዓመት በሆነው ጊዜ ከወንድሞቹ ጋር የአባቱን በጎች ይጠብቅ ነበር፤ እርሱም ከአባቱ ሚስቶች ከባላና ከዘለፋ ልጆች ጋር ሳለ ብላቴና ነበረ፤ ዮሴፍም የክፋታቸውን ወሬ ወደ አባታቸው ወደ እስራኤል ያመጣ ነበር።