ዘፍጥረት 47:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንግዲህ እኛ በፊትህ እንዳንሞት፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ፥ እኛንም፥ ምድራችንንም በእህል ግዛን፤ እኛም ለፈርዖን አገልጋዮች እንሁን፤ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፤ እኛ እንድንድን፥ እንዳንሞትም፥ ምድራችንም እንዳትጠፋ እንዘራ ዘንድ ዘር ስጠን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታዲያ፣ እያየኸን እንዴት እንለቅ? መሬታችንስ ለምን ጠፍ ሆኖ ይቅር? እኛንና መሬታችንን ውሰድና በለውጡ እህል ስጠን፤ እኛ የፈርዖን ገባሮች እንሁን፤ መሬታችንም የርሱ ርስት ይሁን፤ እኛም እንዳንሞት መሬታችንም ጠፍ ሆኖ እንዳይቀር የምንዘራው ዘር ስጠን።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛ በፈትህ ስለምን እንሞታለን? ምድራችንስ ስለምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን፥ እኛም ለፈርዖን ባርያዎች እንሁን፥ ምድራችንም ለእርሱ ትሁን፥ እኛ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኛና ምድራችን በፊትህ እንጥፋን? እኛንና መሬታችንን ገዝተህ እህል ስጠን፤ እኛ የንጉሡ ባሪያዎች እንሆናለን፤ መሬታችንም የእርሱ ይሁን፤ በልተን በሕይወት እንድንኖር እህል ስጠን፤ በመሬታችን ላይ የምንዘራውም ዘር ስጠን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምድራችንስ ስለ ምን ትጠፋለች? እኛንም ምድራችንንም በእህል ግዛን እኛም ለፈርዖን ባሪያዎች እንሁን ምድራችንም ለእርሱ ትሁን እኝ እንድንድን እንዳንሞትም ምድራችንም እንዳትጠፋ ዘር ስጠን። |
ብሩም በግብፅ ምድርና በከነዓን ምድር አለቀ፤ የግብፅ ሰዎችም ሁሉ ወደ ዮሴፍ መጡ፤ እንዲህ ሲሉ፥ “በፊትህ እንዳንሞት እህል ስጠን፤ ብሩ አልቆብናልና።”
ያችም ዓመት ተፈጸመች፤ በሁለተኛዋም ዓመት ወደ እርሱ መጥተው እንዲህ አሉት፥ “እኛ ለጌታችን ሞተን እንዳናልቅበት እህል ስጠን፤ ብሩ በፍጹም አለቀ፤ ንብረታችንና ከብታችንም በጌታችን ዘንድ ነው፤ ከሰውነታችንና ከምድራችን በቀር በጌታችን ፊት አንዳች የቀረን የለም፤
ዮሴፍም የግብፅን ምድር ሁሉ ለፈርዖን ገዛ፤ የግብፅ ሰዎች ሁሉ ራብ ስለጸናባቸው ርስታቸውን ሸጠዋልና፤ ምድሪቱ ለፈርዖን ሆነች።
ካፍ። ሕዝብዋ ሁሉ እንጀራ አጥተው ያለቅሳሉ፤ ሰውነታቸውን ለማበርታት ፍላጎታቸውን ስለ መብል ሰጥተዋል፤ አቤቱ! ተጐሳቍያለሁና እይ፤ ተመልከትም።