ዘፍጥረት 23:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም ተነሣ፤ በሀገሩ ሕዝብ ፊትም ለኬጢ ልጆች ሰገደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም አብርሃም ተነሥቶ የአገሬውን ሕዝብ፣ ኬጢያውያንን እጅ ነሣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም ተነሣ፥ ለምድሩ ሕዝብም፥ በሒታውያን ፊት እጅ ነሣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብርሃም በሒታውያን ፊት እጅ ነሥቶ እንዲህ አለ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም ተነሣ ለምድሩ ሕዝብም ለኬጢ ልጆች ሰገደ። |
ዐይኑንም በአነሣ ጊዜ እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፤ ወደ ምድርም ሰገደ፤
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገደላቸው፤
“አይሆንም፥ ጌታ ሆይ፥ ስማን፤ አንተ ከእግዚአብሔር ዘንድ ለእኛ ንጉሥ ነህና ከመቃብር ስፍራችን በመረጥኸው ቦታ ሬሳህን ቅበር፤ ሬሳህን በዚያ ትቀብር ዘንድ ከእኛ መቃብሩን የሚከለክልህ የለም።”
እንዲህም አላቸው፥ “ሬሳዬን ከፊቴ አርቄ እንድቀብር ከወደዳችሁስ ስሙኝ፤ ለሰዓር ልጅ ለኤፍሮንም ስለ እኔ ንገሩት፤