Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፍጥረት 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 ሁለ​ቱም መላ​እ​ክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰ​ዶም ከተማ በር ተቀ​ምጦ ነበር። ሎጥም ባያ​ቸው ጊዜ ሊቀ​በ​ላ​ቸው ተነሣ፤ ፊቱ​ንም ወደ ምድር ደፍቶ ሰገ​ደ​ላ​ቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 ሁለቱ መላእክት ምሽት ላይ ሰዶም ደረሱ፤ ሎጥም በሰዶም ከተማ መግቢያ በር ተቀምጦ ነበር፤ ሎጥም መላእክቱን ሲያይ ሊቀበላቸው ብድግ አለ፤ በግንባሩም ወደ ምድር ተደፍቶ እጅ ነሣቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፥ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 በዚያኑ ምሽት ሁለቱ መላእክት ወደ ሰዶም መጡ፤ በዚያን ጊዜ ሎጥ በከተማይቱ በር ተቀምጦ ነበር፤ መላእክቱን ባያቸው ጊዜ ሊያነጋግራቸው ከተቀመጠበት ተነሥቶ ሄደ፤ ጐንበስ ብሎም እጅ ነሣቸውና፥

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ አለቸውም

Ver Capítulo Copiar




ዘፍጥረት 19:1
15 Referencias Cruzadas  

ሰዎ​ቹም ከዚያ በተ​መ​ለሱ ጊዜ ወደ ሰዶም መጡ፤ አብ​ር​ሃም ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ገና ቆሞ ነበር።


እን​ግዳ መቀ​በ​ል​ንም አት​ርሱ፤ በዚህ ምክ​ን​ያት ሳያ​ውቁ መላ​እ​ክ​ትን በእ​ን​ግ​ድ​ነት ለመ​ቀ​በል ያታ​ደሉ አሉና።


መጻ​ተ​ኛው ግን በሜዳ አያ​ድ​ርም ነበር፥ ደጄ​ንም ለመ​ጣው ሁሉ እከ​ፍት ነበር፤


በሎጥ ዘመ​ንም ሲበ​ሉና ሲጠጡ፥ ቤት ሲሠ​ሩና ተክል ሲተ​ክሉ፥ ሲሸ​ጡና ሲገዙ ነበረ።


አራ​ንም ሎጥን ወለደ።


እነ​ዚ​ያም ሰዎች ከዚያ ተነ​ሥ​ተው ወደ ሰዶ​ምና ወደ ገሞራ አቀኑ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ሊሸ​ኛ​ቸው አብ​ሮ​አ​ቸው ሄደ፤ አብ​ር​ሃ​ምም ተመ​ልሶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆመ።


አላ​ቸ​ውም፥ “ጌቶች ሆይ፥ ወደ ባሪ​ያ​ችሁ ቤት ገብ​ታ​ችሁ እደሩ፤ እግ​ራ​ች​ሁ​ንም ታጠቡ፤ ነገም ማል​ዳ​ችሁ መን​ገ​ዳ​ች​ሁን ትሄ​ዳ​ላ​ችሁ።” እነ​ር​ሱም፥ “በአ​ደ​ባ​ባዩ እና​ድ​ራ​ለን እንጂ፥ አይ​ሆ​ንም” አሉት።


እጅ​ግም ተጋ​ፉት፤ የደ​ጁ​ንም መዝ​ጊያ ለመ​ስ​በር ቀረቡ። እነ​ዚ​ያም ሰዎች እጃ​ቸ​ውን ዘር​ግ​ተው ሎጥን ወደ እነ​ርሱ ዘንድ ወደ ቤት ስበው አገ​ቡት፤ መዝ​ጊ​ያ​ው​ንም ዘጉት።


አብ​ራም በከ​ነ​ዓን ምድር ተቀ​መጠ፤ ሎጥም በጎ​ረ​ቤት ሕዝ​ቦች ከተማ ተቀ​መጠ፤ ድን​ኳ​ኑ​ንም በሰ​ዶም ተከለ፤


አብ​ር​ሃ​ምም በሀ​ገሩ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰገደ፤


ዮሴ​ፍም ከጕ​ል​በቱ ፈቀቅ አደ​ረ​ጋ​ቸው፤ ወደ ምድ​ርም በግ​ን​ባሩ ሰገደ።


ቦዓዝም ወደ ከተማይቱ በር አደባባይ ወጥቶ በዚያ ተቀመጠ። እነሆም፥ ቦዔዝ ስለ እርሱ ይናገር የነበረው የቅርብ ዘመድ ሲያልፍ ቦዔዝ፦ አንተ ቀርበህ በዚህ ተቀመጥ አለው። እርሱም ቀረብ ብሎ ተቀመጠ።


ወደ ከተ​ማ​ዪቱ ገሥ​ግሼ በወ​ጣሁ ጊዜ፥ በአ​ደ​ባ​ባ​ዩም ወን​በ​ሬን ባኖ​ሩ​ልኝ ጊዜ፥


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios