La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዕዝራ 8:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ስለ​ዚ​ህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ንን፤ እር​ሱ​ም​ሰ​ማን።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ስለዚህ ጾምን፤ ወደ አምላካችንም ስለዚህ ነገር ልመና አቀረብን፤ እርሱም ጸሎታችንን ሰማ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጾምን፥ አምላካችንን ስለዚህ ነገር ለመንን፤ እርሱም ልመናችንን ሰማ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ስለዚህም እግዚአብሔር ራሱ እንዲጠብቀን በጾምና በጸሎት ተማጠንነው፤ እርሱም ጸሎታችንን ሰማ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ስለዚህም ነገር ጾምን፤ ወደ እግዚአብሔርም ለመንን፤ እርሱም ተለመነን።

Ver Capítulo



ዕዝራ 8:23
18 Referencias Cruzadas  

ይስ​ሐ​ቅም ስለ ሚስቱ ርብቃ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለመነ፤ መካን ነበ​ረ​ችና፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰማው፤ ሚስቱ ርብ​ቃም ፀነ​ሰች።


ኢዮ​አ​ካ​ዝም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ለመነ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሶ​ርያ ንጉሥ እስ​ራ​ኤ​ልን ያስ​ጨ​ነ​ቀ​በ​ትን ጭን​ቀት አይ​ቶ​አ​ልና ሰማው።


በሚ​ዋ​ጉ​በ​ትም ጊዜ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ​ዋ​ልና በእ​ር​ሱም ታም​ነ​ዋ​ልና አዳ​ና​ቸው፤ በላ​ያ​ቸ​ውም በረ​ቱ​ባ​ቸው፥ አጋ​ራ​ው​ያ​ንና ከእ​ነ​ርሱ ጋር የነ​በ​ሩ​ትም ሁሉ በእ​ጃ​ቸው ተሰጡ።


በመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ወር በዐ​ሥራ ሁለ​ተ​ኛው ቀን ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እን​ሄድ ዘንድ ከአ​ኅዋ ወንዝ ተነ​ሣን፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም እጅ በላ​ያ​ችን ነበረ፤ በመ​ን​ገ​ድም ከጠ​ላ​ትና ከሚ​ሸ​ምቅ ሰው እጅ አዳ​ነን።


በዚ​ህም ወር በሃያ አራ​ተ​ኛው ቀን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ጾመው፥ ማቅም ለብ​ሰው፥ በራ​ሳ​ቸ​ውም ላይ ትቢያ ነስ​ን​ሰው ተሰ​በ​ሰቡ።


በፍጹም ልብህ በእግዚአብሔር ታምነህ ኑር፥ በራስህም ጥበብ አትደገፍ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ግብ​ፅን በታ​ላቅ መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ታ​ታል፤ ይፈ​ው​ሳ​ታ​ልም፤ ከዚ​ያም በኋላ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይመ​ለ​ሳሉ፤ እር​ሱም ይሰ​ማ​ቸ​ዋል፤ ይፈ​ው​ሳ​ቸ​ው​ማል።


ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመ​ል​ስ​ል​ሃ​ለሁ፤ አን​ተም የማ​ታ​ው​ቀ​ውን ታላ​ቅና ኀይ​ለኛ ነገ​ርን እነ​ግ​ር​ሃ​ለሁ።


ሰማ​ንያ አራት ዓመ​ትም መበ​ለት ሆና ኖረች፤ በጾ​ምና በጸ​ሎ​ትም እያ​ገ​ለ​ገ​ለች፥ ቀንም ሆነ ሌሊት ከቤተ መቅ​ደስ አት​ወ​ጣም ነበር።


ቆር​ኔ​ሌ​ዎ​ስም እን​ዲህ አለው፥ “የዛሬ አራት ቀን በዘ​ጠኝ ሰዓት በዚች ሰዓት በቤቴ ስጸ​ልይ የሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ልብስ የለ​በሰ አንድ ሰው በፊቴ ቆሞ ታየኝ።


ነገር ግን ከዚያ አም​ላ​ካ​ች​ሁን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትሻ​ላ​ችሁ፤ በመ​ከ​ራ​ህም ጊዜ በል​ብ​ህም ሁሉ፥ በነ​ፍ​ስ​ህም ሁሉ​የ​ፈ​ለ​ግ​ኸው እንደ ሆነ ታገ​ኘ​ዋ​ለህ።