አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
መክብብ 7:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጥበብ ጥላ ከብር ጥላ ይሻላል፤ የጥበብንም ዕውቀት ማብዛት ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትሰጠዋለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ገንዘብ ጥላ ከለላ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ጥበብም ጥላ ከለላ ነው፤ የዕውቀት ብልጫዋ ግን፣ ጥበብ የባለቤቷን ሕይወት መጠበቋ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጥበብ ጥላ እንደ ገንዘብ ጥላ ናትና፥ የእውቀትም ብልጫዋ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን መስጠትዋ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጥበብ እንደ ገንዘብ ከለላ ነች፤ ከዚያም በላይ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን ትጠብቃለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጥበብ ጥላ እንደ ገንዘብ ጥላ ናትና፥ የእውቀትም ብልጫዋ ጥበብ ገንዘብ ላደረጋት ሕይወትን እንድትሰጥ ነው። |
አንተ ቤቱን በውስጥም በውጭም፥ በዙሪያው ያለውንም ሁሉ አልሞላህለትምን? የእጁንም ሥራ ባርከህለታል፥ ከብቱንም በምድር ላይ አብዝተህለታል።
በቍጣ ቀን ገንዘብ አይጠቅምም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ታድናለች። ጻድቅ በሞተ ጊዜ ጸጸትን ይተዋል፥ የኀጢአተኛ ሞት ግን በእጅ የተያዘና ሣቅ ይሆናል።
ሰውም ቃሉን ይሰውራል፤ በውኃ እንደሚጠልቅም ይሰወራል፤ ክብሩም በደረቅ ምድር እንደሚፈስስ ውኃ በጽዮን ይገለጣል።
በድኅነታችን መዝገብ በሕግ ይሰበስቡአቸዋል፤ ጥበብና ምክር፥ ጽድቅም ከእግዚአብሔር ዘንድ ናቸው፤ እነዚህም የጽድቅ መዝገቦች ናቸው።
ብቻህን እውነተኛ አምላክ የሆንህ አንተን፥ የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህች የዘለዓለም ሕይወት ናት።
ይህ ነገር ሕይወታችሁ ነው እንጂ ለእናንተ ከንቱ አይደለምና፤ በዚህም ነገር ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ በምትገቡባት ምድር ዘመናችሁ ይረዝማል።”
ክርስቶስን አገለግለው ዘንድ፥ ሁሉን የተውሁለት፥ እንደ ጕድፍም ያደረግሁለት የጌታዬን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና ገናናነት ስለማውቅ ሁሉን እንደ ኢምንት ቈጠርሁት።
ዶግም ዛፎቹን፦ በእውነት እኔን በእናንተ ላይ ካነገሣችሁኝ እሳት ከዶግ ወጥቶ የሊባኖስን ዝግባ ካልበላው ከጥላዬ በታች ታርፉ ዘንድ ኑ አለቻቸው።