Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




መክብብ 2:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እኔም ብር​ሃን ከጨ​ለማ እን​ደ​ሚ​በ​ልጥ እን​ዲሁ ከአ​ላ​ዋቂ ይልቅ ለብ​ልህ ብልጫ እን​ዳ​ለው ተመ​ለ​ከ​ትሁ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ ሁሉ፣ ጥበብም ከሞኝነት እንደሚበልጥ ተመለከትሁ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እኔ ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ እንዲሁ ጥበብ ከአለማወቅ እንደሚበልጥ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እንዲህም አልኩ “በእርግጥ ብርሃን ከጨለማ እንደሚሻል ጥበብም ከሞኝነት መሻልዋን ተመለከትኩ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እኔ ብርሃን ከጨለማ እንደሚበልጥ እንዲሁ ጥበብ ከስንፍና እንዲበልጥ አየሁ።

Ver Capítulo Copiar




መክብብ 2:13
17 Referencias Cruzadas  

ቀድሞ ጨለማ ነበ​ራ​ች​ሁና፥ ዛሬ ግን በጌ​ታ​ችን ብር​ሃን ሆና​ች​ኋል። እን​ግ​ዲ​ህስ እንደ ብር​ሃን ልጆች ተመ​ላ​ለሱ።


ዐይንህ ግን ታማሚ ብትሆን፥ ሰውነትህ ሁሉ የጨለመ ይሆናል። እንግዲህ በአንተ ያለው ብርሃን ጨለማ ከሆነ፥ ጨለማውስ እንዴት ይበረታ!


ብር​ሃን ጣፋጭ ነው፥ ፀሓ​ይ​ንም ማየት ለዐ​ይን መል​ካም ነው።


ተመልሳችሁም በጻድቁና በኃጢአተኛው መካከል፥ ለእግዚአብሔር በሚገዛውና በማይገዛው መካከል ትለያላችሁ።


ከጦር መሣ​ሪ​ያ​ዎች ይልቅ ጥበብ ትሻ​ላ​ለች፤ አንድ ኀጢ​አ​ተኛ ግን ብዙ መል​ካ​ምን ያጠ​ፋል።


እኔም፥ “ከኀ​ይል ይልቅ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች፤ የድ​ሃው ጥበብ ግን ተና​ቀች ቃሉም አል​ተ​ሰ​ማ​ችም” አልሁ።


በከ​ተማ ከሚ​ኖሩ ዐሥር ገዢ​ዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢ​ብን ትረ​ዳ​ዋ​ለች።


ጥበብን ገንዘብ ማድረግ ከወርቅ ይመረጣል። ዕውቀትንም ገንዘብ ማድረግ ከብር ይሻላል።


ምሣሩ ከዛ​ቢ​ያው ቢወ​ልቅ ሰው​የው ፊቱን ወዲ​ያና ወዲህ ይላል፤ ብዙ ኀይ​ልም ያስ​ፈ​ል​ገ​ዋል። ጥበብ ግን ለብ​ርቱ ሰው ትርፉ ነው፤


የዐዋቂዎች ጥበብ መንገዳቸውን ታውቃለች፤ የሰነፎች ስንፍና ግን ወደ ስሕተት ይመራል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios