በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
ዘዳግም 5:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም መካከል ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር፥ ሰውዬው በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህም አላችሁ፤ “አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ግርማውን አሳይቶናል፤ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል። እግዚአብሔር አነጋግሮትም እንኳ፣ ሰው በሕይወት ሊኖር እንደሚችል በዛሬው ቀን አይተናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አላችሁ፦ ‘እነሆ፥ አምላካችን ጌታ ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔር ከሰው ተነጋግሮ ሰውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲህ አላችሁ፦ ‘በእሳት ውስጥ ሆኖ ሲናገር በሰማነው ጊዜ እግዚአብሔር አምላካችን ታላቅነቱንና ክብሩን በግልጥ አሳይቶናል፤ እግዚአብሔር ካነጋገረው በኋላ እንኳ ሰው በሕይወት መኖር እንደሚችል በዛሬው ዕለት አይተናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አላችሁም፦ እነሆ፥ አምላካችን እግዚአብሔር ክብሩንና ታላቅነቱን አሳይቶናል፥ ከእሳቱም ውስጥ ድምፁን ሰምተናል፤ እግዚአብሔርም ከሰው ጋር ሲነጋገር ሰውዬውም በሕይወት ሲኖር ዛሬ አይተናል። |
በዚያም ስፍራ ባረከው። ያዕቆብም፥ “እግዚአብሔርን ፊት ለፊት አየሁ፤ ሰውነቴም ዳነች” ሲል የዚያን ቦታ ስም “ራእየ እግዚአብሔር” ብሎ ጠራው።
እግዚአብሔር ሙሴን አለው፥ “ለያዕቆብ ቤት ለእስራኤልም ልጆች እንዲህ በል፦ እኔ ከሰማይ እንደ ተናገርኋችሁ እናንተ አይታችኋል።
የዚያች ምድር ሰዎች፥ አንተ እግዚአብሔር በዚህ ሕዝብህ መካከል እንደ ሆንህ ሰምተዋል፤ አንተም፥ አቤቱ፥ ዐይን በዐይን እንደሚተያይ ተገልጠህላቸዋል። ደመናህም በላያቸው ቆመች። በቀንም በደመና ዐምድ ፥ በሌሊትም በእሳት ዐምድ በፊታቸው ትሄዳለህ።
አንተ ከእሳት መካከል ሆኖ ሲናገር የሕያው እግዚአብሔርን ድምፅ እንደ ሰማህና በሕይወት እንዳለህ ሌላ ሕዝብ ሰምቶ እንደ ሆነ፥
“እንዲህም ሆነ፤ በእሳት መካከል ድምፁን በሰማችሁ ጊዜ፥ ተራራውም በእሳት ሲነድድ እናንተ፥ የነገዶቻችሁ አለቆች፥ ሽማግሌዎቻችሁም፥ ወደ እኔ ቀረባችሁ፤
አሁንም አንሙት፤ ይህችም ታላቅ እሳት አታጥፋን፤ እኛ የአምላካችን የእግዚአብሔርን ድምፅ ዳግመኛ ብንሰማ እንሞታለን።