“እኔ ከምድር አሕዛብ ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።”
ዘዳግም 4:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ። ይህን ዮርዳኖስንም አልሻገርም፤ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፤ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔም በዚህች ምድር እሞታለሁ፤ ዮርዳኖስን አልሻገርም፤ እናንተ ግን ልትሻገሩ ነው፤ ያችንም መልካም ምድር ትወርሳላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ በዚህች ምድር እሞታለሁና፥ ዮርዳኖስን አልሻገርም፥ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም እኔ የዮርዳኖስን ወንዝ ሳልሻገር በዚህች ምድር እሞታለሁ፤ እናንተ ግን ተሻግራችሁ እነሆ ያቺን ለምለም ምድር ልትወርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን በዚህች ምድር እሞታለሁ፥ ዮርዳኖስንም አልሻገርም፤ እናንተ ግን ትሻገራላችሁ፥ ያችንም መልካሚቱን ምድር ትወርሳላችሁ። |
“እኔ ከምድር አሕዛብ ሁሉ እናንተን ብቻችሁን አውቄአችኋለሁ፤ ስለዚህ ስለ ኀጢአታችሁ ሁሉ እበቀላችኋለሁ።”
እናንተ በጺን ምድረ በዳ በማኅበሩ ጠብ በቃሌ ላይ ዐምፃችኋልና፥ በእነርሱም ፊት በውኃው ዘንድ አላከበራችሁኝምና። ይህም በጺን ምድረ በዳ በቃዴስ ያለው የክርክር ውኃ ነው።”
እኔ እንድሻገርና፥ በዮርዳኖስም ማዶ ያለችውን መልካሚቱን ምድር፥ ያንም መልካሙን ተራራማውን ሀገር አንጢ ሊባኖስንም እንዳይ ፍቀድልኝ።
ይህን ዮርዳኖስን አትሻገርምና ወደ ተራራው ራስ ውጣ፤ ዐይንህንም ወደ ባሕር ወደ መስዕም፥ ወደ አዜብም ወደ ምሥራቅም አንሥተህ በዐይንህ ተመልከት።
እግዚአብሔርም ሙሴን፥ “የምትሞትበት ቀን እነሆ ቀረበ፤ ኢያሱን ጠርተህ እርሱን አዝዘው ዘንድ በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ከእርሱ ጋር ቁም” አለው። ሙሴና ኢያሱም ሄደው በምስክሩ ድንኳን ውስጥ ቆሙ።