La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 34:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ምድረ በዳ​ውን፥ የኢ​ያ​ሪ​ኮን ዙሪያ፥ እስከ ሴይር ዙሪያ ያለ​ው​ንም የፊ​ን​ቆ​ንን ከተማ አሳ​የው፤

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኔጌብንና የዘንባባ ከተማ ከሆነችው ከኢያሪኮ ሸለቆ እስከ ዞዓር ያለውን ምድር ሁሉ ነው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እስከ ጾዓር ድረስ ያለውንም የዘንባባ ዛፎች ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኔጌብንና ሜዳውን፥ የኢያሪኮን ሸለቆ የዘንባባዎች ከተማ የምትባለውን ኢያሪኮን፥ እስከ ጾዓር ድረስ አሳየው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እስከ ዞዓር ድረስ ያለውንም የዘንባባ ዛፎች ያሉባትን ከተማ የኢያሪኮን ሸለቆ ሜዳ አሳየው።

Ver Capítulo



ዘዳግም 34:3
8 Referencias Cruzadas  

ሎጥም ዓይ​ኖ​ቹን አነሣ፤ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ዙሪያ ያለ​ው​ንም ሀገር ሁሉ ውኃ የሞ​ላ​በት መሆ​ኑን አየ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሰዶ​ም​ንና ገሞ​ራን ከማ​ጥ​ፋቱ አስ​ቀ​ድሞ እስከ ሴጎር ድረስ እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ገነ​ትና እንደ ግብፅ ምድር እንደ ነበረ አየ።


ከሰ​ዶም ንጉሥ ከባላ፥ ከገ​ሞራ ንጉሥ ከበ​ርሳ፥ ከአ​ዳማ ንጉሥ ከሰ​ና​አር፥ ከሲ​ባዮ ንጉሥ ከሲ​ም​ቦር፤ ሴጎር ከተ​ባ​ለች ከባላ ንጉ​ሥም ጋር ጦር​ነት አደ​ረጉ።


የሰ​ዶም ንጉ​ሥና የገ​ሞራ ንጉሥ፥ የአ​ዳማ ንጉ​ሥና የሲ​ባ​ዮን ንጉሥ፥ ሴጎር የተ​ባ​ለች የባ​ላቅ ንጉ​ሥም ወጡ፤ እነ​ዚህ ሁሉ በጨው ሸለቆ በእ​ነ​ርሱ ላይ ለሰ​ልፍ ወጡ፤


እን​ግ​ዲህ ፍጠ​ንና በዚያ ራስ​ህን አድን፤ ወደ​ዚያ እስ​ክ​ት​ደ​ርስ ድረስ ምንም አደ​ርግ ዘንድ አል​ች​ል​ምና።” ስለ​ዚ​ህም የዚ​ያች ከተማ ስም ሴጎር ተባለ።


በስ​ማ​ቸ​ውም የተ​ጻፉ ሰዎች ተነ​ሥ​ተው ምር​ኮ​ኞ​ቹን ወሰዱ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም ራቁ​ታ​ቸ​ውን ለነ​በ​ሩት ሁሉ ከም​ር​ኮው አለ​በ​ሱ​አ​ቸው፤ አጐ​ና​ጸ​ፉ​አ​ቸ​ውም፤ ጫማም በእ​ግ​ራ​ቸው አደ​ረ​ጉ​ላ​ቸው፤ መገ​ቡ​አ​ቸ​ውም፤ አጠ​ጡ​አ​ቸ​ውም፤ ቀቡ​አ​ቸ​ውም፤ ደካ​ሞ​ቹ​ንም ሁሉ በአ​ህ​ዮች ላይ አስ​ቀ​መ​ጡ​አ​ቸው፤ ዘን​ባ​ባም ወዳ​ለ​በት ከተማ ወደ ኢያ​ሪኮ ወደ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ቸው አመ​ጡ​አ​ቸው፤ ወደ ሰማ​ር​ያም ተመ​ለሱ።


የአ​ዜቡ ወገን ከጺን ምድረ በዳ በኤ​ዶ​ም​ያስ መያ​ያዣ ይሆ​ናል፤ የአ​ዜ​ብም ዳርቻ ከጨው ባሕር ዳር በም​ሥ​ራቅ በኩል ይጀ​ም​ራል፤


የቄ​ና​ዊው የሙሴ አማት የዮ​ባብ ልጆ​ችም ከዘ​ን​ባባ ከተማ ተነ​ሥ​ተው ከዓ​ራድ በአ​ዜብ በኩል ወዳ​ለው ወደ ይሁዳ ምድረ በዳ ወደ ይሁዳ ልጆች ሄደው ከሕ​ዝቡ ጋር ተቀ​መጡ።


የአ​ሞ​ንን ልጆ​ችና አማ​ሌ​ቅን ወደ እርሱ ሰበ​ሰበ፤ ሄዶም እስ​ራ​ኤ​ልን መታ፤ ዘን​ባባ ያለ​ባ​ት​ንም ከተማ ያዘ።