ዘዳግም 32:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም አለ፦ ፊቴን ከእነርሱ እመልሳለሁ፤ በመጨረሻው ዘመን ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ ጠማማ ትውልድ፥ እምነት የሌላቸው ልጆች ናቸውና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም፣ “ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆንም አያለሁ” አለ፤ ጠማማ ትውልድ፣ የማይታመኑም ልጆች ናቸውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም እንዲህ አለ፦ ‘ጠማማ ትውልድ፥ ያልታመኑም ልጆች ናቸውና፥ ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፥ ፍጻሜያቸው ምን እንደሆነ አያለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ‘ፊቴን ከእነርሱ እሰውራለሁ፤ መጨረሻቸው ምን እንደሚሆን አያለሁ፤ እነርሱ የተበላሸ ትውልድ እምነት የሚጣልባቸው ልጆች አይደሉም’ አለ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም አለ፦ ፊቴን እሰውርባቸዋለሁ፤ 2 ፍጻሜያቸው ምን እንደ ሆነ አያለሁ፤ 2 ጠማማ ትውልድ፥ 2 ያልታመኑም ልጆች ናቸው። |
እግዚአብሔርም በእስራኤል ዘር ሁሉ ተቈጣ፤ አስጨነቃቸውም፤ ከፊቱም እስኪጥላቸው ድረስ በበዝባዦች እጅ አሳልፎ ሰጣቸው።
እግዚአብሔርም በባሪያዎቹ በነቢያት ሁሉ አፍ እንደ ተናገረው እስራኤልን ከፊቱ እስኪያወጣ ድረስ ከእርስዋ አልራቁም። እስራኤልም እስከ ዛሬ ድረስ ከምድሩ ወደ አሦር ፈለሰ።
ማልደውም ተነሡ፤ ወደ ቴቁሔም ምድረ በዳ ወጡ፤ ሲወጡም ኢዮሣፍጥ ቆመና፥ “ይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሆይ፥ ስሙኝ፤ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ በነቢዩም እመኑ፤ ነገሩም ይቀናላችኋል” አለ።
ስምህንም የሚጠራ፥ አንተንም የሚያስብ የለም፤ ፊትህንም ከእኛ መልሰሃል፤ ለኀጢአታችንም አሳልፈህ ሰጥተኸናል።
ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእጃቸው ያጨበጭባሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ይወድዳሉ፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?
ኢየሱስም መልሶ “የማታምን ጠማማ ትውልድ ሆይ! እስከ መቼ ከእናንተ ጋር እኖራለሁ? እስከ መቼስ እታገሣችኋለሁ? ወደዚህ ወደ እኔ አምጡት፤” አለ።
ከሞትሁ በኋላ ፈጽማችሁ እንድትረክሱ፥ ካዘዝኋችሁም መንገድ ፈቀቅ እንድትሉ አውቃለሁና። በእጃችሁም ሥራ ታስቈጡት ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ስላደረጋችሁ፥ በኋለኛው ዘመን ክፉ ነገር ያገኛችኋል።”
እግዚአብሔርም፦ ውጡ፤ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ በአምላካችሁ በእግዚአብሔር ቃል ዐመፃችሁ፤ በእርሱም አላመናችሁም፤ ቃሉንም አልሰማችሁም።
ያለ እምነትም እግዚአብሔርን ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚቀርብ ሰው አስቀድሞ እግዚአብሔር እንዳለ፥ ለሚሹትም ዋጋ እንደሚሰጣቸው ሊያምን ይገባዋል።