“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
ዘዳግም 26:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከቅዱስ ማደርያህ ከሰማይ ጐብኝ፤ ሕዝብህንም እስራኤልን፥ ወተትና ማር የምታፈስሰውን ምድር ትሰጠን ዘንድ ለአባቶቻችን እንደ ማልህላቸው የሰጠሃቸውንም ምድር ባርክ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለአባቶቻችን በመሐላ ቃል በገባኸው መሠረት፣ ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ባርክ።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንና ለእኛ የሰጠኸንን ይህችን ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለአባቶቻችን በቃልህ እንደገባኸው መሓላ መሠረት ባርክ።’ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሰማይ ካለው ቅዱስ መኖሪያህ ሆነህ ወደ ታች ተመልከት፤ ሕዝብህን እስራኤልንም ባርክ፤ ለቀድሞ አባቶቻችን በገባኸው ቃል መሠረት የሰጠኸንን በማርና በወተት የበለጸገችውን ለም ምድር ባርክ።’ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከቅዱስ ማደሪያህ ከሰማይ ጐብኝ፥ ሕዝብህንም እስራኤልን ለአባቶቻችን እንደ ማልህላቸው የሰጠኸንንም ወተትና ማር የምታፈስሰውን አገር ባርክ። |
“በውኑ እግዚአብሔር ከሰው ጋር በምድር ላይ ይኖራልን? እነሆ ሰማይ ከሰማያትም በላይ ያለው ሰማይ ይይዝህ ዘንድ አይችልም፤ ይልቁንስ እኔ ለስምህ የሠራሁት ቤት እንዴት ያንስ!
አንተ በማደሪያህ በሰማይ ስማ፤ የምድርም አሕዝብ ሁሉ ስምህን ያውቁ ዘንድ፥ እንደ ሕዝብህ እንደ እስራኤል ይፈሩህ ዘንድ፥ በዚህም በሠራሁት ቤት ስምህ እንደ ተጠራ ያውቁ ዘንድ፥ እንግዳው የሚለምንህን ሁሉ አድርግ።
ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምፃቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ ማደሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።
ለዘለዓለም በአርያም የሚኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱሳን የሆነ፥ በቅዱሳን አድሮ የሚኖር፥ ለተዋረዱት ትዕግሥትን የሚሰጥ፥ ልባቸውም ለተቀጠቀጠ ሕይወትን የሚሰጥ ልዑል እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦
የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፤ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና፤ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን፥ ለታሰሩትም መፈታትን፥ ለዕውራንም ማየትን እናገር ዘንድ ልኮኛል።
ከሰማይ ተመለስ፤ ከቅድስናህና ከክብርህ ማደሪያም ተመልከት፤ ቅንአትህና ኀይልህስ ወዴት ነው? የቸርነትህና የይቅርታህ ብዛት ወዴት ነው? ቸል ብለሃልና።
የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “ምርኮአቸውን በመለስሁ ጊዜ በይሁዳ ሀገር በከተሞችዋ፦ የጽድቅ ማደሪያ ሆይ! የቅድስና ተራራ ሆይ! እግዚአብሔር ይባርክህ የሚል ነገርን እንደ ገና ይናገራሉ።
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ሰማይ ዙፋኔ ነው፤ ምድርም የእግሬ መረገጫ ናት፤ ምን ዐይነት ቤት ትሠሩልኛላችሁ? የማርፍበት ቦታስ ምን ዐይነት ቦታ ነው?
እነሆ፥ ምድሪቱን ሰጠኋችሁ፤ ግቡ፥ እግዚአብሔር ለእነርሱ፥ ከእነርሱም በኋላ ለዘራቸው ይሰጣት ዘንድ ለአባቶቻችሁ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም የማለላቸውን ምድር ውረሱ።
በኀዘኔም ጊዜ እኔ ከእርሱ አልበላሁም፤ ለርኩስም ነገር ከእርሱ የኀጢአት መሥዋዕት አልሠዋሁም፤ ከእርሱም አንዳች ለሞተ ሰው አልሰጠሁም፤ የአምላኬንም የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቼአለሁ፤ ያዘዝኸኝንም ሁሉ አድርጌአለሁ።
ወደ አባቶቻችንም አምላክ ወደ እግዚአብሔር ጮኽን፤ እግዚአብሔርም ቃላችንን ሰማ፤ ጭንቀታችንንም፥ ድካማችንንም፥ ግፋችንንም አየ፤
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፦ ማርና ወተት የምታፈስሰውን ምድር ይሰጥህ ዘንድ የአባቶችህ አምላክ እግዚአብሔር እንደ ተናገረ እጅግ እንድትበዛ፥ መልካምም እንዲሆንልህ ታደርጋት ዘንድ ጠብቅ።” ከግብፅ ምድር ከወጡ በኋላ ሙሴ ለእስራኤል ልጆች በምድረ በዳ ያዘዛቸው ሥርዐትና ፍርድ ሁሉ ይህ ነው።