ዘዳግም 22:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “የወንድምህ በሬ ወይም በግ በመንገድ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ እነርሱን መልሰህ ለወንድምህ ስጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታየው፣ ወደ እርሱ መልሰህ አምጣለት እንጂ ዝም ብለህ አትለፈው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፥ ወደ ወንድምህ መልሰው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “የእስራኤላዊ ወገንህ ንብረት የሆነ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ሲባዝን ብታገኝ ዝም ብለህ አትለፈው፤ ወደ ባለቤቱ መልሰህ ውሰድለት፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የወንድምህ በሬ ወይም በግ ጠፍቶ ብታይ ቸል አትበል፤ ወደ ወንድምህ መልሰው። |
ለተራበውም እንጀራህን አጥግበው፤ ድሆችን ወደ ቤትህ አስገብተህ አሳድራቸው፤ የተራቈተውንም ብታይ አልብሰው፤ ከሥጋ ዘመድህ አትሸሽግ።
የጠፋውንም እፈልጋለሁ፤ የባዘነውንም እመልሳለሁ፤ የተሰበረውንም እጠግናለሁ፤ የደከመውንም አጸናለሁ፤ የወፈረውንና የበረታውንም እጠብቃለሁ፤ በፍርድም እጠብቃቸዋለሁ።”
የደከመውን አላጸናችሁትም፤ የታመመውንም አልፈወሳችሁትም፤ የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም፤ የባዘነውንም አልመለሳችሁትም፤ የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም፤ በኀይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።
ዘሩንም ለሞሎክ ሲሰጥ፥ የሀገሩ ሕዝብ ያን ሰው ቸል ቢሉት፥ አይተው እንዳላዩ ቢሆኑ፥ ባይገድሉትም፥ እኔ በዚያ ሰውና በቤተ ሰቡ ላይ ፊቴን አከብዳለሁ።
ወይም የጠፋውን ነገር ቢያገኝ፥ ስለዚህም ቢዋሽ፥ ሰው ኀጢአትን ለመሥራት ከሚያደርጋቸው ከእነዚህ ነገሮች ሁሉ በአንዲቱ በሐሰት ቢምል፥
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ተናግሮአል፦ እውነተኛውን ፍርድ ፍረዱ፣ ቸርነትንና ምሕረትን ሁላችሁ ለወንድሞቻችሁ አድርጉ፣ መበለቲቱንና ደሀ አደጉን፥
“እህልህን በምታበራይበት ጊዜ የበሬውን አፉን አትሰረው።” እንግዲህ ይህን የጻፈ ለእግዚአብሔር በሬ አሳዝኖት ነውን?
ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘሃቸው ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻቸው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣሉ፤ ለእርሱም ትመልስለታለህ።