የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለአባቱ ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገልጋዮቹን ወደ ሰሎሞን ላከ።
ዘዳግም 20:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰላም ቃልም ቢመልሱልህ ደጅም ቢከፍቱልህ፥ በከተማው ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገብሩልህ፤ አገልጋዮችም ይሁኑህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ፣ በከተማዪቱ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከተቀበሉህና ደጃቸውን ከከፈቱልህ በከተማዋ ውስጥ ሕዝብ ሁሉ ገባርህ ይሁን፤ ያገልግልህም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የቅጽር በሮቻቸውን ከፍተው እንዲገብሩ የሰላም ድርድርህን ቢቀበሉ በከባድ ሥራ ያገልግሉህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዕርቅ ቃልም ቢመልሱልህ ደጅም ቢከፍቱልህ፥ በከተማ ውስጥ ያለው ሕዝብ ሁሉ ይገብሩልህ ያገልግሉህም። |
የጢሮስ ንጉሥ ኪራም ለአባቱ ለዳዊት በዘመኑ ሁሉ ወዳጁ ስለ ነበረ፥ ሰሎሞን በአባቱ ፋንታ ንጉሥ ለመሆን እንደ ተቀባ ሰምቶ አገልጋዮቹን ወደ ሰሎሞን ላከ።
እርሱም፥ “በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸውን ግደል እንጂ በሰይፍህና በቀስትህ የማረክሃቸው አይደሉምና አትግደላቸው። ይልቁንስ እንጀራና ውኃ በፊታቸው አቅርብላቸው፤ በልተውና ጠጥተውም ወደ ጌታቸው ይመለሱ” አለው።
በጋዜርም የተቀመጡትን ከነዓናውያንን ኤፍሬም አላጠፋቸውም፤ እስከ ዛሬም ድረስ ከነዓናውያን በኤፍሬም መካከል ተቀምጠዋል፤ ገባርም ሆኑ።
በዚያም ቀን ኢያሱ እነርሱን ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ እንጨት ቈራጮችና ውኃ ቀጂዎች አደረጋቸው። ስለዚህም የገባዖን ሰዎች ለማኅበሩና ለእግዚአብሔር መሠዊያ፥ እግዚአብሔርም ለመረጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እንጨት ቈራጮች፥ ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።
ኢያሱንም፥ “እኛ ባሪያዎችህ ነን፤ ከሩቅ ሀገርም ነን” አሉት። ኢያሱም፥ “እናንተ እነማን ናችሁ? ከወዴትስ መጣችሁ?” አላቸው።
እነርሱም አሉት፥ “በአምላክህ በእግዚአብሔር ስም እጅግ ከራቀ ሀገር ባሪያዎችህ መጥተናል፤ ዝናውንም፥ በግብፃውያንም ያደረገውን ሁሉ፥