በዐመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር ቢቆም፥
ተንኰለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ቢከስስ፣
ተንኰለኛ የሆነ ምስክር አንድን ሰው በሐሰት ቢከስ፥
አንድ ክፉ ሰው ሌላውን ሰው በሐሰት ወንጅሎ ቢከሰው፥
በዓመፃ ይከስሰው ዘንድ በሰው ላይ ሐሰተኛ ምስክር ቢቆም፥
የትዕቢት እግር አይምጣብኝ፥ የኀጢአተኛ እጅም አያውከኝ።
የታመነ ምስክር አይዋሽም፤ የሐሰት ምስክር ግን ሐሰትን ያቀጣጥላል።
ሐሰተኛ ምስክር ሳይቀጣ አይቀርም፥ በግፍዕ የሚከስም አያመልጥም።
የሐሰት ምስክሮችንም አቆሙበት፤ እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “ይህ ሰው በዚህ ቤተ መቅደስ ላይና በኦሪት ላይ የስድብ ቃል እየተናገረ ዝም በል ቢሉት እንቢ አለ፤
“በባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር፤ ምስክርንም አታሳብል።