La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 19:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ምድ​ራ​ቸ​ውን የሚ​ሰ​ጥ​ህን አሕ​ዛብ ባጠ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸ​ውም ጊዜ፥ በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በቤ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ በሚደመስሳቸው ጊዜና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፣

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

“አምላክህ ጌታ ምድራቸውን ለአንተ የሚሰጥባቸውን አሕዛብ ጌታ እግዚአብሔር በሚደመስሳቸውና አንተም እነርሱን አስለቅቀህ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸው በምትቀመጥበት ጊዜ፥

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

“እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር የሚኖሩትን ሕዝቦች ደምስሶ ከተሞቻቸውንና ቤቶቻቸውንም ወርሰህ በዚያ መኖር በምትጀምሩበት ጊዜ፥

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አምላክህ እግዚአብሔር ምድራቸውን የሚሰጥህን አሕዛብ ባጠፋ ጊዜ፥ በወረስሃትም ጊዜ፥ በከተሞቻቸውና በቤቶቻቸውም በተቀመጥህ ጊዜ፥

Ver Capítulo



ዘዳግም 19:1
11 Referencias Cruzadas  

ሳይ​ፈ​ቅድ ቢመ​ታው፥ ባይ​ሸ​ም​ቅ​በ​ትም፥ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድን​ገት በእጁ ቢጥ​ለው፥ ገዳዩ የሚ​ሸ​ሽ​በ​ትን ስፍራ እኔ አደ​ር​ግ​ል​ሃ​ለሁ።


እነሆ፥ ወደ ከነ​ዓን ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ላ​ችሁ፤ ባላ​ማ​ወቅ ነፍስ የገ​ደለ ወደ​ዚያ ይሸሽ ዘንድ የመ​ማ​ፀኛ ከተ​ሞች እን​ዲ​ሆ​ኑ​ላ​ችሁ ከተ​ሞ​ችን ለእ​ና​ንተ ለዩ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


“በም​ድር ላይ በም​ት​ኖ​ሩ​በት ዘመን ሁሉ የአ​ባ​ቶ​ቻ​ችሁ አም​ላክ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሷት ዘንድ በሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ሀገር ታደ​ር​ጉት ዘንድ የም​ት​ጠ​ብ​ቁት ሥር​ዐት፥ ፍር​ድም ይህ ነው።


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ትወ​ር​ሳ​ቸው ዘንድ የም​ት​ሄ​ድ​ባ​ቸ​ውን አሕ​ዛብ በፊ​ትህ ባጠፋ ጊዜ፥ አን​ተም በወ​ረ​ስ​ሃ​ቸው ጊዜ፥ በም​ድ​ራ​ቸ​ውም በተ​ቀ​መ​ጥህ ጊዜ፥ ከፊ​ትህ ከጠፉ በኋላ እነ​ር​ሱን ለመ​ከ​ተል እን​ዳ​ትሻ፥


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ርስት አድ​ርጎ ወደ​ሚ​ሰ​ጥህ ምድር በገ​ባህ፥ በወ​ረ​ስ​ሃ​ትም ጊዜ፥ በተ​ቀ​መ​ጥ​ህ​ባ​ትም ጊዜ፦ በዙ​ሪ​ያዬ እን​ዳ​ሉት አሕ​ዛብ ሁሉ በላዬ አለቃ እሾ​ማ​ለሁ ብትል፥


“አም​ላ​ክህ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለአ​ንተ ሊሰ​ጣት ለአ​ባ​ቶ​ችህ ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ወደ ማለ​ላ​ቸው ምድር ባገ​ባህ ጊዜ፤ ያል​ሠ​ራ​ሃ​ቸ​ው​ንም ታላ​ቅና መል​ካም ከተ​ሞች፥


ያል​ሞ​ላ​ሃ​ቸ​ው​ንም ሀብ​ትን የሞሉ ቤቶች፥ ያል​ማ​ስ​ሃ​ቸ​ው​ንም የተ​ማሱ ጕድ​ጓ​ዶች፥ ያል​ተ​ከ​ል​ሃ​ቸ​ው​ንም ወይ​ንና ወይራ በሰ​ጠህ ጊዜ፥ በበ​ላ​ህና በጠ​ገ​ብ​ህም ጊዜ፤


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ኢያ​ሱን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ያል​ደ​ከ​ማ​ች​ሁ​በ​ት​ንም ምድር፥ ያል​ሠ​ራ​ች​ኋ​ቸ​ው​ንም ከተ​ሞች ሰጠ​ኋ​ችሁ፤ ተቀ​መ​ጣ​ች​ሁ​ባ​ቸ​ውም፤ ካል​ተ​ከ​ላ​ች​ኋ​ቸ​ውም ከወ​ይ​ንና ከወ​ይራ በላ​ችሁ።’