ዘዳግም 17:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልቡም እንዳይስት ሚስቶችን ለእርሱ አያብዛ፤ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያብዛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልቡ እንዳይስትም ብዙ ሚስቶችን አያግባ፤ ብዙ ብርና ወርቅም አያግበስብስ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞም ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት ማድረግ እግዚአብሔርን ከመከተል ስለሚገታው ንጉሡ ብዙ ሚስቶች እንዲኖሩት አያስፈልገውም፤ ወርቅና ብርም በብዛት አያከማች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልቡም እንዳይስት ሚስቶችን ለእርሱ አያበዛም፤ ወርቅና ብርም ለእርሱ እጅግ አያበዛም። |
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከቤትህ ክፉ ነገርን አስነሣብሃለሁ፤ ሚስቶችህንም በዐይኖችህ እያየህ እወስዳለሁ፤ ለዘመድህም እሰጣቸዋለሁ፤ በዚችም ፀሐይ ፊት ከሚስቶችህ ጋር ይተኛል።
ዳዊትም ከኬብሮን ከመጣ በኋላ እንደ ገና ቁባቶቹንና ሚስቶቹን ከኢየሩሳሌም ወሰደ፤ ለዳዊትም ደግሞ ወንዶችና ሴቶች ልጆች ተወለዱለት።
ንጉሡም ሰሎሞን ያሠራው የመጠጫ ዕቃ ሁሉ ወርቅ ነበረ፤ ኵስኵስቱም የወርቅ ነበረ፤ የሊባኖስ ዱር የተባለውን የዚያን ቤት ዕቃ ሁሉ በወርቅ አስለበጠው። የብርም ዕቃ አልነበረም፤ በሰሎሞን ዘመን የብር ዋጋ ዝቅተኛ ነበርና።
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ እንዲበዛ አደረገው፤ የዝግባም እንጨት ብዛት በቆላ እንደሚበቅል ሾላ ሆነ።
ንጉሡም ብሩንና ወርቁን፥ በኢየሩሳሌም እንደ ድንጋይ፥ የዝግባንም እንጨት በብዛት በቆላ እንደሚገኝ ሾላ በይሁዳ አኖረ።
ሮብዓምም ከሚስቶቹና ከቁባቶቹ ሁሉ ይልቅ የአቤሴሎምን ልጅ መዓካን ወደደ፤ ዐሥራ ስምንትም ሚስቶችና ስድሳ ቁባቶች ነበሩት፤ ሃያ ስምንት ወንዶችና ስድሳ ሴቶች ልጆችንም ወለደ።
የእስራኤል ንጉሥ ሰሎሞን በዚህ ነገር ኀጢአት አድርጎ የለምን? በብዙ አሕዛብም መካከል እንደ እርሱ ያለ ንጉሥ አልነበረም፤ በአምላኩም ዘንድ የተወደደ ነበረ፤ እግዚአብሔርም በእስራኤል ሁሉ ላይ አንግሦት ነበር፤ እርሱንም እንኳ እንግዶች ሴቶች አሳቱት።
እግዚአብሔር የሕይወትን መንፈስ አንድ አድርጎ ጠብቆልን የለምን? እርሱም የሚፈልገው ምንድር ነው? ዘር አይደለምን? ስለዚህ መንፈሳችሁን ጠብቁ፥ ማንም የልጅነት ሚስቱን አያታልል።
በአሁኑ ዘመን ባለ ጠጎች የሆኑት የትዕቢትን ነገር እንዳያስቡ ደስም እንዲለን ሁሉን አትርፎ በሚሰጠን በሕያው እግዚአብሔር እንጂ፥ በሚያልፍ ባለ ጠግነት ተስፋ እንዳያደርጉ እዘዛቸው።
ዳሩ ግን ባለ ጠጎች ሊሆኑ የሚፈልጉ በጥፋትና በመፍረስ ሰዎችን በሚያሰጥምና በሚያሰንፍ በሚጎዳም በብዙ ምኞትና በፈተና በወጥመድም ይወድቃሉ።