La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




አሞጽ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ን​ተና ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ሁት ወገን ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ይህን ቃል ስሙ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብጽ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ባወጣችሁ፥ በእናንተ በመላው ሕዝብ ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፥

Ver Capítulo



አሞጽ 3:1
18 Referencias Cruzadas  

ባሪ​ያ​ዎቹ የእ​ስ​ራ​ኤል ዘር፥ ለእ​ር​ሱም የተ​መ​ረ​ጣ​ችሁ የያ​ዕ​ቆብ ልጆች ሆይ፥


እን​ዲ​ህም አለ፥ “ይሁዳ ሁሉ፥ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም የም​ት​ኖሩ፥ አን​ተም ንጉሡ ኢዮ​ሣ​ፍጥ! ስሙ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ች​ኋል፦ ሰልፉ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው እንጂ የእ​ና​ንተ አይ​ደ​ለ​ምና ከዚህ ታላቅ ወገን የተ​ነሣ አት​ፍሩ፤ አት​ደ​ን​ግ​ጡም።


እና​ንተ የያ​ዕ​ቆብ ቤት ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ቤት ቅሬታ ሁሉ፥ ከማ​ኅ​ፀ​ንም ጀምሮ የተ​ሸ​ከ​ም​ኋ​ችሁ፥ ከሕ​ፃ​ን​ነ​ትም ጀምሮ ያስ​ተ​ማ​ር​ኋ​ችሁ፥ ስሙኝ።


ያዕ​ቆብ ሆይ፥ የጠ​ራ​ሁ​ህም እስ​ራ​ኤል ሆይ፥ ስማኝ፤ እኔ ፊተ​ኛው ነኝ፤ እኔም ዘለ​ዓ​ለ​ማዊ ነኝ።


መታ​ጠ​ቂያ በሰው ወገብ ላይ እን​ደ​ም​ት​ጣ​በቅ፥ እን​ዲሁ ለስም፥ ለመ​መ​ኪ​ያና ለክ​ብር ሕዝብ ይሆ​ኑ​ልኝ ዘንድ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ቤት ሁሉ፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ቤት ሁሉ ከእኔ ጋር አጣ​ብ​ቄ​አ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ነገር ግን አል​ሰ​ሙም።”


በዚያ ዘመን ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ ለእ​ስ​ራ​ኤል ወገ​ኖች ሁሉ አም​ላክ እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝብ ይሆ​ኑ​ኛል።


እኔም ባሳ​ደ​ድ​ኋ​ቸው ስፍራ ሁሉ የቀሩ፥ ከዚ​ህች ክፉ ትው​ልድ የተ​ረፉ ቅሬ​ቶች ሁሉ፥ ከሕ​ይ​ወት ይልቅ ሞትን ይመ​ር​ጣሉ።”


እና​ንተ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሆይ! እው​ነ​ትና ምሕ​ረት፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ማወቅ በም​ድር ስለ​ሌለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ድር ላይ የሚ​ኖ​ሩ​ትን ይወ​ቅ​ሳ​ልና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ካህ​ናት ሆይ! ይህን ስሙ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! አድ​ምጡ፤ የን​ጉሥ ቤት ሆይ! ልብ አድ​ርጉ፤ ለሚ​መ​ለ​ከት ወጥ​መድ፥ በታ​ቦ​ርም ላይ የተ​ዘ​ረጋ አሽ​ክላ ሆና​ች​ኋ​ልና ፍርድ በእ​ና​ንተ ላይ ነው።


የአ​ሞ​ራ​ዊ​ው​ንም ምድር ትወ​ርሱ ዘንድ ከግ​ብፅ ምድር አወ​ጣ​ኋ​ችሁ፤ በም​ድረ በዳም አርባ ዓመት መራ​ኋ​ችሁ።


በሰ​ማ​ርያ ተራራ የም​ት​ኖሩ፥ ድሆ​ች​ንም የም​ት​በ​ድሉ፥ ችግ​ረ​ኞ​ች​ንም የም​ታ​ስ​ጨ​ንቁ፥ ጌቶ​ቻ​ቸ​ው​ንም፦ አምጡ እን​ጠጣ የም​ትሉ እና​ንተ የባ​ሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! በእ​ና​ንተ ላይ ለሙሾ የማ​ነ​ሣ​ውን ይህን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


እንዲህም አልሁ፦ የያዕቆብ አለቆችና የእስራኤል ቤት ገዦች ሆይ፥ እባካችሁ ስሙኝ፥ ፍርድን ታውቁ ዘንድ አይገባችሁምን?


በባሕር ዳር ለሚኖሩ ለከሊታውያን ሕዝብ ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፥ የእግዚአብሔር ቃል በአንተ ላይ ነው፥ የሚቀመጥብህም ሰው እንዳይኖር አጠፋሃለሁ።


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚለውን ጆሮ ያለው ይስማ።