Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




አሞጽ 3:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 የእስራኤል ልጆች ሆይ፤ እግዚአብሔር በእናንተ ከግብጽ ባወጣሁት ሕዝብ ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ በእናንተ ላይ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የእስራኤል ሕዝብ ሆይ! ከግብጽ ባወጣችሁ፥ በእናንተ በመላው ሕዝብ ላይ እግዚአብሔር የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 የእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሆይ! እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በእ​ና​ን​ተና ከግ​ብፅ ምድር በአ​ወ​ጣ​ሁት ወገን ሁሉ ላይ የተ​ና​ገ​ር​ሁ​ትን ይህን ቃል ስሙ፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1 የእስራኤል ልጆች ሆይ፥ እግዚአብሔር በእናንተ፥ ከግብጽ ምድር ባወጣሁት ወገን ሁሉ ላይ የተናገረውን ይህን ቃል ስሙ፥

Ver Capítulo Copiar




አሞጽ 3:1
18 Referencias Cruzadas  

እናንተ የባሪያው የእስራኤል ዘሮች፣ እናንተ የተመረጣችሁ የያዕቆብ ልጆች።


እርሱም እንዲህ አለ፤ “ንጉሥ ኢዮሣፍጥ፣ እናንተም በይሁዳና በኢየሩሳሌም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ! እግዚአብሔር እንዲህ ይላችኋል፤ ‘ውጊያው የእግዚአብሔር እንጂ የእናንተ አይደለምና፣ ከዚህ ታላቅ ሰራዊት የተነሣ አትፍሩ፤ አትደንግጡ።


“እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ የእስራኤል ቤት ቅሬታ ሁሉ፣ ከተፀነሳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የያዝኋችሁ፣ ከተወለዳችሁበት ጊዜ ጀምሮ የተሸከምኋችሁ ስሙኝ።


“ያዕቆብ ሆይ፤ የጠራሁህ እስራኤል ሆይ፤ ስማኝ፤ እኔ እኔው ነኝ፤ ፊተኛው እኔ ነኝ፤ ኋለኛውም እኔ ነኝ።


መቀነት በሰው ወገብ ላይ እንደሚታሰር፣ መላው የእስራኤልና የይሁዳ ቤት ከእኔ ጋራ ተጣብቆ ለስሜ ምስጋናና ክብር፣ የእኔ ሕዝብ እንዲሆንልኝ አድርጌው ነበር፤ ሕዝቤ ግን አልሰማም’ ይላል እግዚአብሔር።


“በዚያ ዘመን” ይላል እግዚአብሔር፤ “ለእስራኤል ነገድ ሁሉ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”


ከዚህ ክፉ ሕዝብ የተረፉት ሁሉ፣ ባሳደድኋቸው ስፍራ ሁሉ ከሕይወት ይልቅ ሞትን ይመርጣሉ፤ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር።’


እናንተ የእስራኤል ልጆች፣ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ እግዚአብሔር በምድሪቱ በምትኖሩት ላይ የሚያቀርበው ክስ አለውና፤ ምክንያቱም ታማኝነት የለም፤ ፍቅርም የለም፤ እግዚአብሔርንም ማወቅ በምድሪቱ የለም።


“እናንተ ካህናት፤ ይህን ስሙ! የእስራኤል ቤት፤ አስተውሉ! የንጉሥ ቤት ሆይ፤ አድምጡ! ይህ ፍርድ በእናንተ ላይ ነው፤ በምጽጳ ወጥመድ፣ በታቦርም ላይ የተዘረጋ መረብ ሆናችኋልና።


የአሞራውያንን ምድር ልሰጣችሁ፣ ከግብጽ አወጣኋችሁ፤ አርባ ዓመትም በምድረ በዳ መራኋችሁ።


እናንተ በሰማርያ ተራራ የምትኖሩ የባሳን ላሞች፤ ድኾችን የምትጨቍኑና ችግረኞችን የምታስጨንቁ፣ ባሎቻችሁንም፣ “መጠጥ አቅርቡልን” የምትሉ ሴቶች ይህን ቃል ስሙ፤


የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ስለ እናንተ የምደረድረውን ይህን የሙሾ ቃል ስሙ፤


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም። ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤ የመከራ ጊዜ ይሆናልና።


ከዚያም እኔ እንዲህ አልሁ፤ “እናንተ የያዕቆብ መሪዎች፤ እናንተ የእስራኤል ቤት ገዦች ስሙ፤ ፍትሕን ማወቅ አይገባችሁምን?


እናንተ በባሕር ዳርቻ የምትኖሩ፣ የከሊታውያን ሰዎች ሆይ፤ ወዮላችሁ! የፍልስጥኤማውያን ምድር ከነዓን ሆይ፤ በአንቺ ላይ የተነገረው የእግዚአብሔር ቃል ይህ ነው፤ “ፍጹም አጠፋሻለሁ፤ ከነዋሪዎችሽም የሚተርፍ የለም።”


መንፈስ ለአብያተ ክርስቲያናት የሚናገረውን ጆሮ ያለው ይስማ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos