ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
ሐዋርያት ሥራ 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳውል ግን እየበረታ ሔደ፤ በደማስቆም ለነበሩት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደ ሆነ እያስረዳ መልስ አሳጣቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆ ለሚኖሩትም አይሁድ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ መሆኑን ማስረጃ እያቀረበ አፋቸውን ያስይዛቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፤ በደማስቆም ለተቀመጡት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደሆነ አስረድቶ መልስ ያሳጣቸው ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳውል ግን ይበልጥ እየበረታ ሄደ፤ ኢየሱስ መሲሕ መሆኑን በማስረዳት በደማስቆ ይኖሩ የነበሩትን አይሁድ መልስ ያሳጣቸው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳውል ግን እየበረታ ሄደ፥ በደማስቆም ለተቀመጡት አይሁድ ይህ ክርስቶስ እንደ ሆነ አስረድቶ መልስ ያሳጣቸው ነበር። |
ነገር ግን ቀስቶቻቸው በኀይል ተቀጠቀጡ፤ የእጆቻቸው ክንድ ሥርም በያዕቆብ ኀያል እጅ ዛለ፤ በዚያም በአባትህ አምላክ ዘንድ እስራኤልን አጸናው።
ክርስቶስ እንዲሞት ከሙታንም ተለይቶ እንዲነሣ፥ እየተረጐመና እየአስተማራቸው፥ “ይህ እኔ የነገርኋችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው” ይል ነበር።
ሲላስና ጢሞቴዎስም ከመቄዶንያ በወረዱ ጊዜ ጳውሎስ፥ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደ ሆነ ለአይሁድ እየመሰከረ ቃሉን በማስተማር ይተጋ ነበር።
ከዚህም በኋላ ወደ እርሱ የሚመጡበትን ቀን ቀጠሩትና ብዙዎች ወዳረፈበት ወደ እርሱ መጡ፤ ከጥዋትም ጀምሮ እስከ ማታ ድረስ ስለ እግዚአብሔር መንግሥት እየመሰከረ ስለ ጌታችን ስለ ኢየሱስም ከሙሴ ኦሪትና ከነቢያት እየጠቀሰ ነገራቸው።
የሰሙትም ሁሉ አደነቁ፤ እንዲህም አሉ፥ “በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ሁሉ ይጠላቸው የነበረው ይህ አይደለምን? ስለዚህ ወደዚህ የመጣው እያሰረ ወደ ሊቀ ካህናቱ ሊወስዳቸው አይደለምን?”
በርናባስም አግኝቶ ወደ ሐዋርያት ወሰደው፤ ጌታችንም በመንገድ እንደ ተገለጠለትና እንደ አነጋገረው፥ በደማስቆም በኢየሱስ ስም እንደ አስተማረ ነገራቸው።
ነገር ግን እግዚአብሔር ጥበበኞችን ሊያሳፍር የዚህን ዓለም ሰነፎች መረጠ፤ ኀይለኞችንም ያሳፍር ዘንድ እግዚአብሔር የዚህን ዓለም ደካሞች መረጠ።