ከኤላም ልጆች ወገን የነበረውም የኢያሔል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “አምላካችንን በድለናል፤ የምድርንም አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ።
ሐዋርያት ሥራ 27:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁንም እላችኋለሁ፤ መርከባችን እንጂ ከመካከላችን አንድ ሰው ስንኳ አይጠፋምና አትፍሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሁንም ቢሆን አይዟችሁ፤ መርከቧ እንጂ ከእናንተ አንዲት ነፍስ እንኳ አትጠፋምና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁንም አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አሁንም መርከቡ ብቻ ይጐዳል እንጂ ከእናንተ በማንም ላይ ጥፋት አይደርስም፤ ስለዚህ አይዞአችሁ፤ አትፍሩ! ብዬ እመክራችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁንም፦ አይዞአችሁ ብዬ እመክራችኋለሁ፤ ይህ መርከብ እንጂ ከእናንተ አንድ ነፍስ እንኳ አይጠፋምና። |
ከኤላም ልጆች ወገን የነበረውም የኢያሔል ልጅ ሴኬንያ ዕዝራን እንዲህ ብሎ ተናገረው፥ “አምላካችንን በድለናል፤ የምድርንም አሕዛብ እንግዶች ሴቶችን አግብተናል፤ አሁን ግን ስለዚህ ነገር ገና ለእስራኤል ተስፋ አለ።
በሁለተኛዪቱም ሌሊት ጌታችን ለጳውሎስ ተገልጦ፥ “ጽና፥ በኢየሩሳሌም ምስክር እንደ ሆንኸኝ እንዲሁ በሮም ምስክር ትሆነኛለህ” አለው።
ጳውሎስም ይህን ባየ ጊዜ ለመቶ አለቃውና ለወታደሮቹ፥ “እነዚህ ቀዛፊዎች በመርከብ ውስጥ ከሌሉ መዳን አትችሉም” አላቸው።
የቀሩትም በመርከቡ ስብርባሪ ዕንጨትና በሳንቃው ላይ ተሻገሩ፤ ሌሎችም በመርከቡ ገመድ ላይ እየተንጠላጠሉ ተሻገሩ፤ ሁሉም እንዲህ ባለ ሁኔታ በደኅና ወደ ምድር ደረሱ።
ስለ ወንዶችና ስለ ሴቶች ልጆቻቸውም የሕዝቡ ሁሉ ልብ አዝኖ ነበርና ሕዝቡ ሊወግሩት ስለ ተናገሩ ዳዊት እጅግ ተጨነቀ፤ ዳዊት ግን በአምላኩ በእግዚአብሔር ራሱን አጽናና።