La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ሐዋርያት ሥራ 16:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱም ትእ​ዛ​ዙን ተቀ​ብሎ ወደ ውስ​ጠ​ኛው ወኅኒ ቤት አስ​ገ​ባ​ቸው፤ እግ​ራ​ቸ​ው​ንም በግ​ንድ አጣ​ብቆ ጠረ​ቃ​ቸው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም ይህን የመሰለ ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፣ ወደ ወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገብቶ እግራቸውን ከግንድ ጋራ አጣብቆ አሰራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፤ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ጠባቂው ይህን ትእዛዝ ከተቀበለ በኋላ፥ በወህኒ ቤቱ ውስጠኛ ክፍል አስገባቸው፤ እግሮቻቸውንም በግንድና ግንድ መካከል አጣብቆ አሰራቸው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱም የዚህን ዓይነት ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ውስጠኛው ወኅኒ ጣላቸው፥ እግራቸውንም በግንድ አጣብቆ ጠረቃቸ።

Ver Capítulo



ሐዋርያት ሥራ 16:24
11 Referencias Cruzadas  

ንጉሡ እን​ዲህ ይላል፦ በደ​ኅና እስ​ክ​መ​ለስ ድረስ ይህን ሰው በግ​ዞት አኑ​ሩት፤ የመ​ከ​ራም እን​ጀራ መግ​ቡት፤ የመ​ከ​ራም ውኃ አጠ​ጡት በሉ​አ​ቸው” አለ።


አሳም በነ​ቢዩ በአ​ናኒ ላይ ተቈጣ፤ ስለ​ዚ​ህም ነገር ተቈ​ጥ​ቶ​አ​ልና በግ​ዞት አኖ​ረው፤ በዚ​ያን ጊዜም አሳ ከሕ​ዝቡ አያሌ ሰዎ​ችን አስ​ጨ​ነቀ።


እግ​ሮ​ች​ንም በድጥ አሰ​ነ​ካ​ከ​ልህ፥ ሥራ​ዬ​ንም ሁሉ መር​ም​ረ​ሃል፤ እግ​ሬም በቆ​መች ጊዜ ተው​ኸኝ።


እግ​ሬን በግ​ንድ አጣ​በቀ፥ መን​ገ​ዴ​ንም ሁሉ ጠበቀ።


በማ​ኅ​በ​ራ​ቸው እሳት ነደ​ደች፥ ነበ​ል​ባ​ልም ኃጥ​ኣ​ንን አቃ​ጠ​ላ​ቸው።


ትን​ቢት የሚ​ና​ገ​ረ​ውን ሰው ሁሉ፥ የሚ​ለ​ፈ​ል​ፈ​ው​ንም ሰው ሁሉ በግ​ዞት ታኖ​ረ​ውና በፈ​ሳ​ሽም ታሰ​ጥ​መው ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አለቃ እን​ድ​ት​ሆን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በካ​ህኑ በዮ​ዳሄ ፋንታ ካህን አድ​ር​ጎ​ሃል።


አንተ በዚያ እሞት ዘንድ ወደ ዮና​ታን ቤት አት​መ​ል​ሰኝ ብዬ በን​ጉሡ ፊት ለመ​ንሁ” በላ​ቸው።


ኤር​ም​ያ​ስ​ንም ወሰ​ዱት፤ በግ​ዞት ቤትም አደ​ባ​ባይ ወደ ነበ​ረው ወደ ንጉሡ ልጅ ወደ መል​ክያ ጕድ​ጓድ ውስጥ ጣሉት፤ ኤር​ም​ያ​ስ​ንም በገ​መድ አወ​ረ​ዱት። በጕ​ድ​ጓ​ዱም ውስጥ ጭቃ እንጂ ውኃ አል​ነ​በ​ረ​በ​ትም፤ ኤር​ም​ያ​ስም ወደ ጭቃው ውስጥ ገባ።