2 ተሰሎንቄ 3:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! የጌታ ቃል እንዲሮጥ፥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዐመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በቀረውስ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ ዘንድ እንደ ሆነው የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲሠራጭና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! በእናንተ መካከል እንደ ሆነው ሁሉ የጌታ ቃል ፈጥኖ እንዲስፋፋና እንዲከበር ስለ እኛ ጸልዩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በመጨረሻም ወንድሞች ሆይ! በእናንተ ዘንድ እንደሆነው ሁሉ የጌታ ቃል በፍጥነት እንዲስፋፋና እንዲከበር ለእኛ ጸልዩልን፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በቀረውስ፥ ወንድሞች ሆይ፥ የጌታ ቃል እንዲሮጥ በእናንተም ዘንድ ደግሞ እንደሚሆን እንዲከበር፥ እምነትም ለሁሉ ስለማይሆን ከዓመፀኞችና ከክፉዎች ሰዎች እንድንድን ስለ እኛ ጸልዩ። |
ጌታችን ኢየሱስም አላቸው፥ “መከሩ ብዙ ነው፤ ሠራተኛው ግን ጥቂት ነው፤ እንግዲህ ለመከሩ ሠራተኛ ጨምሮ ይልክ ዘንድ ባለ መከሩን ለምኑት።
የእግዚአብሔርም ቃል ከፍ ከፍ አለ፤ በኢየሩሳሌምም ምእመናን እጅግ በዙ፤ ከካህናትም መካከል ያመኑ ብዙዎች ነበሩ።
ወንድሞች፥ በጸሎታችሁ ስለ እኔ ወደ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ትተጉ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ፍቅር እማልዳችኋለሁ።
ወድሞቻችን ሆይ፥ እንግዲህ ደስ ይበላችሁ፤ ጽኑ፤ ታገሡ፤ በአንድ ልብም ሁኑ፤ በሰላም ኑሩ፤ የሰላምና የፍቅር አምላክም ከእናንተ ጋር ይሁን።
ስለ እርሱ የታሰርሁለትን የእግዚአብሔርን ምሥጢር እንድንናገር፥ እግዚአብሔር የቃሉን በር ይከፍትልን ዘንድ ለእኛም ደግሞ ጸልዩልን፤ ለምኑልንም፤
ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።
ከእናንተ ወጥቶ የጌታ ቃል በመቄዶንያና በአካይያ ብቻ አልተሰማምና፤ ነገር ግን ምንም እንድንናገር እስከማያስፈልግ ድረስ፥ በእግዚአብሔር ዘንድ የሚሆን እምነታችሁ በሁሉ ስፍራ ተወርቶአል።
ስለዚህም የመልእክትን ቃል እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ከእኛ በተቀበላችሁ ጊዜ፥ በእውነት እንዳለ በእናንተ በምታምኑ ደግሞ እንደሚሠራ እንደ እግዚአብሔር ቃል እንጂ እንደ ሰው ቃል አድርጋችሁ ስላልተቀበላችሁት፥ እኛ ደግሞ እግዚአብሔርን ሳናቋርጥ እናመሰግናለን።
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! ልትመላለሱ እግዚአብሔርንም ደስ ልታሰኙ እንዴት እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ እንደ ተቀበላችሁ፥ እናንተ ደግሞ እንደምትመላለሱ፥ ከፊት ይልቅ ትበዙ ዘንድ በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችሁማለን።