La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 17:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የአ​ቤ​ሴ​ሎ​ምም አገ​ል​ጋ​ዮች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥ​ተው፥ “አኪ​ማ​ሆ​ስና ዮና​ታን የት አሉ?” አሉ፤ ሴቲ​ቱም፥ “ፈፋ​ውን ተሻ​ግ​ረው ሄዱ፤ ጥቂ​ትም ቀደ​ሙ​አ​ችሁ” አለ​ቻ​ቸው። እነ​ር​ሱም ፈል​ገው አጡ​አ​ቸው፤ ወደ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ተመ​ለሱ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፣ “አኪማአስና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቁ። ሴቲቱም፣ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፣ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአቤሴሎም ሰዎች እዚያ ቤት ወደ ሴቲቱ ዘንድ መጥተው፥ “አሒማዓጽና ዮናታን የት አሉ?” ብለው ጠየቋት። ሴቲቱም፥ “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ብላ መለሰችላቸው፤ እነርሱም ፈልገው ስላጧቸው፥ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የአቤሴሎም ባለሟሎች ወደዚያ ቤት መጥተው ሴቲቱን “አሒማዓጽና ዮናታን የት ናቸው?” ሲሉ ጠየቁአት። እርስዋም “ወንዙን ተሻግረው ሄደዋል” ስትል መለሰች። ሰዎቹም ፈልገው ሊያገኙአቸው ስላልቻሉ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የአቤሴሎም ባሪያዎች ወደ ሴቲቱ ወደ ቤት መጥተው፦ አኪማአስና ዮናታን የት አሉ? አሉ፥ ሴቲቱም፦ ፈፋውን ተሻግረው ሄዱ አለቻቸው። እነርሱም ፈልገው ባላገኙአቸው ጊዜ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 17:20
9 Referencias Cruzadas  

ወደ ከተማ ግን ተመ​ል​ሰህ ለአ​ቤ​ሴ​ሎም፦ ወን​ድ​ሞ​ችህ፥ ንጉ​ሡም መጡ። እነሆ፥ በኋ​ላዬ ናቸው። ንጉሥ ሆይ፥ አገ​ል​ጋ​ይህ ነኝ፤ አስ​ቀ​ድሞ ለአ​ባ​ትህ አገ​ል​ጋይ ነበ​ርሁ፥ እን​ዲሁ አሁ​ንም ለአ​ንተ አገ​ል​ጋይ ነኝ፥ ተወኝ ልኑር ብት​ለው የአ​ኪ​ጦ​ፌ​ልን ምክር ትለ​ው​ጥ​ል​ኛ​ለህ።


አዋ​ላ​ጆ​ችም ፈር​ዖ​ንን፥ “የዕ​ብ​ራ​ው​ያን ሴቶች እንደ ግብፅ ሴቶች ስላ​ል​ሆኑ አዋ​ላ​ጆች ሳይ​ገቡ ይወ​ል​ዳሉ” አሉት።


“አት​ስ​ረቁ፤ አት​ዋ​ሹም፤ ባል​ን​ጀ​ራ​ው​ንም የሚ​ቀማ አይ​ኑር።


እር​ሱም፥ “ከድ​ን​ኳኑ ደጃፍ ቁሚ፤ ሰውም መጥቶ፦ ‘በዚህ ሰው አለን?’ ብሎ ቢጠ​ይ​ቅሽ አንቺ፦ ‘የለም’ ትዪ​ዋ​ለሽ” አላት።


ዳዊ​ትም ካህ​ኑን አቤ​ሜ​ሌ​ክን፥ “የተ​ላ​ክ​ህ​በ​ትን ነገ​ርና የሰ​ጠ​ሁ​ህን ትእ​ዛዝ ማንም አይ​ወቅ ብሎ ንጉሡ አንድ ነገር አዝ​ዞ​ኛል፤ ስለ​ዚ​ህም ‘ብላ​ቴ​ኖቼን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መታ​መን’ በሚ​ባ​ለው እን​ዲህ ባለው ስፍራ እን​ዲ​ሆኑ አዝ​ዣ​ቸ​ዋ​ለሁ።