2 ነገሥት 8:6 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቃት፤ እርስዋም ነገረችው። ንጉሡም ከባለሟሎቹ አንዱን ሰጣት፤ “እህልዋንና ገንዘብዋን ሁሉ ሀገሩን ከተወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታዋን ሁሉ መልስላት” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንጉሡም ስለ ስለዚሁ ጕዳይ ጠየቃትና ነገረችው። ከዚያም ንጉሡ፣ “የነበራትን ሁሉ እንዲሁም ትታ ከሄደችበት ጊዜ አንሥቶ እስካሁን ድረስ ያለውን የዕርሻዋን ሰብል በሙሉ እንድትመልስላት” ሲል አንድ ሹም አዘዘላት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ግያዝ ለንጉሡ የሰጠውን መልስ ሴትዮዋ ለንጉሡ እውነት መሆኑን አረጋገጠችለት፤ ስለዚህም ንጉሡ አንድ ባለ ሥልጣን ጠርቶ፥ የእርሷ የሆነው ማናቸውም ነገርና እንዲሁም የእርሻ መሬትዋ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስገኘው የእህል ሰብል ጭምር እንዲመለስላት ትእዛዝ ሰጠላት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ግያዝ ለንጉሡ የሰጠውን መልስ ሴትዮዋ ለንጉሡ እውነት መሆኑን አረጋገጠችለት፤ ስለዚህም ንጉሡ አንድ ባለሥልጣን ጠርቶ፥ የእርስዋ የሆነው ማናቸውም ነገርና እንዲሁም የእርሻ መሬትዋ በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ያስገኘው የእህል ሰብል ጭምር እንዲመለስላት ትእዛዝ ሰጠላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቀ፤ ነገረችውም። ንጉሡም “የነበረላትን ሁሉ፥ መሬትዋንም ከተወች ጀምራ እስከ ዛሬ ድረስ ያለውን የእርሻዋን ፍሬ ሁሉ መልስላት፤” ብሎ ስለ እርስዋ ጃንደረባውን አዘዘ። |
ዳዊትም፥ “ስለ አባትህ ስለ ዮናታን ቸርነት ፈጽሜ አደርግልሃለሁና አትፍራ፤ የአባትህን አባት የሳኦልን መሬት ሁሉ እመልስልሃለሁ፤ አንተም ሁል ጊዜ ከገበታዬ እንጀራን ትበላለህ” አለው።
እርሱም የሞተውን ሕፃን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ።
ኤልሳዕም ወደ ደማስቆ ሄደ፤ የሶርያም ንጉሥ ወልደ አዴር ታምሞ ነበር፤ “የእግዚአብሔር ሰው ወደዚህ መጥቶአል” ብለውም ነገሩት።
ፊቱንም አቅንቶ በመስኮቱ አያት። “አንቺ ማን ነሽ? ወደዚህ ወደ እኔ ውረጂ” አላት። ከዚህም በኋላ ሁለት ጃንደረቦች ወደ እርሱ ተመለከቱ።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ወንድምህም በአቅራቢያህ ባይሆን ወይም ባታውቀው ይዘሃቸው ወደ ቤትህ ትገባለህ፤ ወንድምህ እስኪሻቸው ድረስ በአንተ ዘንድ ይቀመጣሉ፤ ለእርሱም ትመልስለታለህ።
የአሞንም ልጆች ንጉሥ የዮፍታሔን መልእክተኞች፥ “እስራኤል ከግብፅ በወጣ ጊዜ ከአርኖን ጀምሮ እስከ ያቦቅና እስከ ዮርዳኖስ ድረስ ምድሬን ስለ ወሰደ ነው፤ አሁንም በሰላም መልሱልኝ” ብሎ መለሰላቸው።