2 ነገሥት 8:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱም የሞተውን ሕፃን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ያች ሴት መጥታ ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ወደ ንጉሥ ጮኸች፥ ግያዝም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ፥ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኤልሳዕ ልጇን ከሞት ያስነሣላት ሴት ስለ ቤቷና ስለ መሬቷ ለማመልከት ወደ ንጉሡ ዘንድ የቀረበችውም፣ ኤልሳዕ የሞተውን ልጅ እንዴት እንዳስነሣ ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ወቅት ነበር። ግያዝም፣ “ንጉሥ ጌታዬ ሆይ፤ ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣው ልጇም ይህ ነው” አለ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጇ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኤልሳዕ የሞተ ሰው ማስነሣቱን ግያዝ ለንጉሡ በሚነግርበት ጊዜ ሴቲቱ መጥታ አቤቱታዋን ለንጉሡ አቀረበች፤ ግያዝ “ንጉሥ ሆይ! ሴትዮዋ እነሆ፥ ይህች ናት፤ ኤልሳዕ ከሞት ያስነሣውም ልጅዋ ይሄ ነው!” በማለት ለንጉሡ አስረዳ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርሱም የሞተውን እንደ አስነሣ ለንጉሡ ሲናገር፥ እነሆ፥ ልጅዋን ያስነሣላት ሴት ስለ ቤትዋና ስለ መሬትዋ ወደ ንጉሥ ጮኸች፤ ግያዝም “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! ሴቲቱ ይህች ናት፤ ኤልሳዕም ያስነሣው ልጅዋ ይህ ነው፤” አለ። |
ተመልሶም በቤቱ ውስጥ አንድ ጊዜ ወዲህና ወዲያ ተመላለሰ፤ ደግሞም ወጥቶ ሰባት ጊዜ በሕፃኑ ላይ ተጋደመ፤ ከዚያም በኋላ ሕፃኑ ዐይኖቹን ከፈተ።
ከአገልጋዮቹም አንዱ፥ “ጌታዬ ሆይ፥ በእስራኤል ሀገር ነቢዩ ኤልሳዕ ያለ አይደለምን? በእልፍኝህ ውስጥ ሆነህ የምትናገረውንና ቃልህን ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ እርሱ ይነግረዋል፤” አለ።
ንጉሡም ሴቲቱን ጠየቃት፤ እርስዋም ነገረችው። ንጉሡም ከባለሟሎቹ አንዱን ሰጣት፤ “እህልዋንና ገንዘብዋን ሁሉ ሀገሩን ከተወች ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የሄደ ቦታዋን ሁሉ መልስላት” አለው።
እኔም ተመለስሁ፥ ከፀሓይ በታችም ሩጫ ለፈጣኖች፥ ጦርነትም ለኀያላን፥ እንጀራም ለጠቢባን፥ ባለጠግነትም ለአስተዋዮች፥ ሞገስም ለዐዋቂዎች እንዳልሆነ አየሁ፤ ጊዜና ዕድል ግን ሁሉን ያገናኛቸዋል።
ሳኦልም የዳዊት ድምፅ እንደ ሆነ ዐውቆ፥ “ልጄ ዳዊት ሆይ! ይህ ድምፅህ ነውን?” አለው። ዳዊትም፥ “ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! አዎ እኔ ባሪያህ ነኝ” አለው።