2 ነገሥት 23:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮአቄምም በነገሠ ጊዜ ሃያ አምስት ዓመት ሆኖት ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ሄልድፍ ትባል ነበር፤ እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። እናቱ ዘቢዳ ትባላለች፤ እርሷም የሩማ ተወላጅ የፈዳያ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ሀያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፐዳያ ልጅ ነበረች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢዮአቄም በይሁዳ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖርያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እናቱም ዘቢዳ ተብላ የምትጠራ የሩማ ከተማ ተወላጅ የሆነው የፐዳያ ልጅ ነበረች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘቢዳ ትባል ነበር፤ እርስዋም የሩማ ሰው የፈዳያ ልጅ ነበረች። |
ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጐልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱም ዘካራ የምትባል የኔሬያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበረች፤ አባቶቹም እንዳደረጉ በአምላኩ በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ። 5 ‘ሀ’ በእነዚያም ወራት የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ወደዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገዛለት። ከእርሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግዚአብሔርም የከለዳውያንንና የሶርያውያንን፥ የሞዓባውያንንና የአሞናውያንን ልጆችና የሰማርያን አደጋ ጣዮች ላከበት፤ ከዚህም በኋላ በአገልጋዮቹ በነቢያት እንደ ተነገረው እንደ እግዚአብሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለሠራቸው ኀጢአቶችና ኢዮአቄም ስላፈሰሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየሩሳሌምንም በንጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእግዚአብሔር ቍጣ በይሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግዚአብሔርም ሊያጠፋቸው አልፈለገም ነበር።
በይሁዳም ንጉሥ በኢዮስያስ ልጅ በኢዮአቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮስያስ ልጅ እስከ ሴዴቅያስ እስከ ዐሥራ አንደኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየሩሳሌም እስከ ተማረከችበት እስከ አምስተኛው ወር ድረስ መጣ።
ስለዚህ እግዚአብሔር ስለ ይሁዳ ንጉሥ ስለ ኢዮስያስ ልጅ ስለ ኢዮአቄም እንዲህ ይላል፥ “ወንድሜ ሆይ፥ ወዮ! ጌታዬ ሆይ፥ ወዮ! እያለ የሚያለቅስለት ለሌለው ለዚያ ሰው ወዮለት!