Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




2 ዜና መዋዕል 36:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ኢዮ​አ​ቄ​ምም መን​ገሥ በጀ​መረ ጊዜ የሃያ አም​ስት ዓመት ጐል​ማሳ ነበረ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እና​ቱም ዘካራ የም​ት​ባል የኔ​ሬ​ያሳ ልጅ የራማ ሴት ነበ​ረች፤ አባ​ቶ​ቹም እን​ዳ​ደ​ረጉ በአ​ም​ላኩ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ አደ​ረገ። 5 ‘ሀ’ በእ​ነ​ዚ​ያም ወራት የባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ናቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ወደ​ዚያ ሀገር መጣና ሦስት ዓመት ተገ​ዛ​ለት። ከእ​ር​ሱም ከዳ። 5 ‘ለ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የከ​ለ​ዳ​ው​ያ​ን​ንና የሶ​ር​ያ​ው​ያ​ንን፥ የሞ​ዓ​ባ​ው​ያ​ን​ንና የአ​ሞ​ና​ው​ያ​ንን ልጆ​ችና የሰ​ማ​ር​ያን አደጋ ጣዮች ላከ​በት፤ ከዚ​ህም በኋላ በአ​ገ​ል​ጋ​ዮቹ በነ​ቢ​ያት እንደ ተነ​ገ​ረው እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ራቁ። 5 ‘ሐ’ ነገር ግን ምናሴ ስለ​ሠ​ራ​ቸው ኀጢ​አ​ቶ​ችና ኢዮ​አ​ቄም ስላ​ፈ​ሰ​ሰው ንጹሕ ደም፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌ​ም​ንም በን​ጹሕ ደም ስለ ሞላት ከፊቱ ይርቁ ዘንድ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣ በይ​ሁዳ ላይ ነበር። 5 ‘መ’ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ቸው አል​ፈ​ለ​ገም ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ኢዮአቄም በነገሠ ጊዜ፣ ዕድሜው ሃያ ዐምስት ዓመት ነበር፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ። በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ ነገር አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሀያ አምስት ዓመት ጎልማሳ ነበረ፥ በኢየሩሳሌምም ዐሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በጌታ ፊት ክፉ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ኢዮአቄም በይሁዳ ላይ በነገሠ ጊዜ ዕድሜው ኻያ አምስት ዓመት ነበር፤ መኖሪያውንም በኢየሩሳሌም አድርጎ ዐሥራ አንድ ዓመት ገዛ፤ እርሱም ኃጢአት በመሥራቱ አምላኩን እግዚአብሔርን አሳዘነ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ኢዮአቄምም መንገሥ በጀመረ ጊዜ የሃያ አምስት ዓመት ጕልማሳ ነበረ፤ በኢየሩሳሌምም አሥራ አንድ ዓመት ነገሠ፤ በአምላኩም በእግዚአብሔር ፊት ክፉ አደረገ።

Ver Capítulo Copiar




2 ዜና መዋዕል 36:5
11 Referencias Cruzadas  

በይ​ሁ​ዳም ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን፥ እስከ ይሁዳ ንጉሥ እስከ ኢዮ​ስ​ያስ ልጅ እስከ ሴዴ​ቅ​ያስ እስከ ዐሥራ አን​ደ​ኛው ዓመት ፍጻሜ፥ ኢየ​ሩ​ሳ​ሌም እስከ ተማ​ረ​ከ​ች​በት እስከ አም​ስ​ተ​ኛው ወር ድረስ መጣ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም መን​ግ​ሥት መጀ​መ​ሪያ ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ መጣ፤ አለም፦


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም ዘመን ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ የመጣ ቃል ይህ ነው፤ እን​ዲህ ሲል፦


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት ይህ ቃል ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወደ ኤር​ም​ያስ እን​ዲህ ሲል መጣ።


በይ​ሁዳ ንጉሥ በኢ​ዮ​ስ​ያስ ልጅ በኢ​ዮ​አ​ቄም በአ​ራ​ተ​ኛው ዓመተ መን​ግ​ሥት እነ​ዚ​ህን ቃላት ከኤ​ር​ም​ያስ አፍ በመ​ጽ​ሐፍ በጻ​ፋ​ቸው ጊዜ፥ ነቢዩ ኤር​ም​ያስ ለኔ​ርዩ ልጅ ለባ​ሮክ የተ​ና​ገ​ረው ቃል ይህ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos