La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 22:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጸሓ​ፊው ሳፋ​ንም ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ የሕግ መጽ​ሐፍ ሰጥ​ቶ​ኛል” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያም ጸሓፊው ሳፋን ለንጉሡ፣ “ሊቀ ካህናቱ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል” ብሎ ነገረው። ሳፋንም ለንጉሡ ከመጽሐፉ አነበበለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከዚያም ቀጠል በማድረግ፥ “ካህኑ ሒልቂያ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ ይኸው” ብሎ ለንጉሡ አነበበለት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚያም ቀጠል በማድረግ፥ “ካህኑ ሒልቂያ አግኝቶ የሰጠኝ መጽሐፍ ይኸው” ብሎ ለንጉሡ አነበበለት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ጸሐፊው ሳፋንም ለንጉሡ “ካህኑ ኬልቅያስ መጽሐፍ ሰጥቶኛል፤” ብሎ ነገረው። ሳፋንም በንጉሡ ፊት አነበበው።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 22:10
17 Referencias Cruzadas  

ንጉ​ሡም የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ ቃል በሰማ ጊዜ ልብ​ሱን ቀደደ።


ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ወደ ንጉሡ መጣ፤ ለን​ጉ​ሡም፥ “በመ​ቅ​ደሱ የተ​ገ​ኘ​ውን ገን​ዘብ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ አፈ​ሰ​ሱት፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቤት ሥራ ለመ​ሥ​ራት ለተ​መ​ደ​ቡት ሰዎች ሰጡት” ብሎ ነገ​ረው።


ጸሓ​ፊ​ውም ሳፋን ለን​ጉሡ፥ “ካህኑ ኬል​ቅ​ያስ መጽ​ሐፍ ሰጠኝ” ብሎ ነገ​ረው። ሳፋ​ንም በን​ጉሡ ፊት አነ​በ​በው።


በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።


ከመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ውም ቀን ጀምሮ እስከ መጨ​ረ​ሻው ቀን ድረስ ዕለት ዕለት የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ሕግ መጽ​ሐፍ ያነ​ብብ ነበር። በዓ​ሉ​ንም ሰባት ቀን ያህል አደ​ረጉ፤ በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን እንደ ሕጋ​ቸው ወጡ።


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


በቃሉ የም​ት​ን​ቀ​ጠ​ቀጡ ሆይ፥ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ስሙ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ስም ይከ​ብር ዘንድ፦ ደስ​ታ​ች​ሁም ይገ​ለጥ ዘንድ፥ እነ​ር​ሱም ያፍሩ ዘንድ የሚ​ጠ​ሏ​ች​ሁ​ንና የሚ​ጸ​የ​ፉ​አ​ች​ሁን ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በሏ​ቸው።


ለነ​ገ​ሥ​ታ​ቱና ለመ​ኳ​ን​ንቱ፦ የክ​ብ​ራ​ችሁ አክ​ሊል ከራ​ሳ​ችሁ ወር​ዶ​አ​ልና ራሳ​ች​ሁን አዋ​ር​ዳ​ችሁ ተቀ​መጡ በላ​ቸው።


ሚክ​ያ​ስም ባሮክ በሕ​ዝቡ ጆሮ በመ​ጽ​ሐፉ በአ​ነ​በበ ጊዜ የሰ​ማ​ውን ቃል ሁሉ ነገ​ራ​ቸው።


እነ​ር​ሱም፥ “እስኪ ተቀ​መጥ፤ በጆ​ሮ​አ​ች​ንም አን​ብብ” አሉት። ባሮ​ክም በጆ​ሮ​አ​ቸው አነ​በ​በው።


ንጉ​ሡም ክር​ታ​ሱን ያመጣ ዘንድ ይሁ​ዳን ላከ፤ እር​ሱም ከጸ​ሓ​ፊው ከኤ​ሊ​ሳማ ክፍል ወሰ​ደው፤ ይሁ​ዳም በን​ጉ​ሡና በን​ጉሡ አጠ​ገብ በቆ​ሙት አለ​ቆች ሁሉ ጆሮ አነ​በ​በው።


አንተ ግን ገብ​ተህ ከአፌ የጻ​ፍ​ኸ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በጾም ቀን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት በሕ​ዝቡ ጆሮ በክ​ር​ታሱ አን​ብብ፤ ደግ​ሞም ከከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸው በሚ​ወጡ በይ​ሁዳ ሰዎች ሁሉ ጆሮ አን​ብ​በው።