2 ነገሥት 16:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንጉሡም አካዝ፥ “የሚቃጠለውን የጥዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሕዝቡንም ሁሉ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን፥ የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ፥ የሌላውንም መሥዋዕታቸውን ደም ሁሉ በእርሱ ላይ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን በየጥዋቱ ለእኔ ይሁን” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ንጉሥ አካዝ፣ ካህኑን ኦርያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “በዚህ በትልቁ አዲስ መሠዊያ ላይ የጧቱን የሚቃጠል መሥዋዕትና የማታውን የእህል ቍርባን፣ የንጉሡን የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን እንዲሁም የመላውን የአገሪቱን ሕዝብ የሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህልና የመጠጥ ቍርባናቸውን አቅርብ፤ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ደምና የሌላውን መሥዋዕት ደም ሁሉ በመሠዊያው ላይ ርጨው፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ መመሪያ ለመጠየቅ የምጠቀምበት ይሆናል።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኡሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠውትንም የእንስሶች ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኡሪያን እንዲህ ሲል አዘዘው፤ “ይህን የእኔን ታላቅ መሠዊያ ማለዳ ለሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕት፥ በምሽት ለሚቀርበውም የእህል መባ ስለ ንጉሡና ስለ ሕዝቡ የሚቀርበው የሚቃጠል መሥዋዕትና የእህል መባ የሚቀርብበትና የሕዝቡ የወይን ጠጅ መባ የሚፈስበት እንዲሆን አድርግ፤ የሚሠዉትንም የእንስሶች ደም ሁሉ በእርሱ ላይ አፍስስ፤ ከነሐስ የተሠራው መሠዊያ ግን እኔ ራሴ የምፈልገውን ነገር የምጠይቅበት እንዲሆን አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንጉሡ አካዝም “የሚቃጠለውን የጠዋት መሥዋዕት፥ የማታውንም የእህሉን ቍርባን፥ የንጉሡንም የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ ለአገሩም ሕዝብ የሚሆን የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን የመጠጡንም ቍርባን በታላቁ መሠዊያ ላይ አቅርብ፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት ደም ሁሉ የሌላ መሥዋዕቱንም ደም ሁሉ ርጭበት፤ የናሱ መሠዊያ ግን እኔ እጠይቅበት ዘንድ ይሁን፤” ብሎ ካህኑን ኦርያን አዘዘው። |
ገባዖን ፈጽማ ትሰፋ ነበርና በዚያ መሥዋዕት ይሠዋ ዘንድ ተነሥቶ ሄደ፤ ሰሎሞንም በዚያ መሠዊያ ላይ በገባዖን አንድ ሺህ የሚቃጠል መሥዋዕት ሠዋ።
በእግዚአብሔር ፊት ያለው የናሱ መሠዊያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ ይይዝ ዘንድ ታናሽ ስለ ነበረ፥ በዚያ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና የእህሉን ቍርባን፥ የሰላሙንም መሥዋዕት ስብ አሳርጎአልና በእግዚአብሔር ቤት ፊት የነበረውን የአደባባዩን መካከል ንጉሡ በዚያ ቀን ቀደሰ።
በእግዚአብሔርም ፊት የነበረውን የናሱን መሠዊያ ከእግዚአብሔር ቤት ፊት ከመሠዊያውና ከእግዚአብሔር ቤት መካከል ፈቀቅ አድርጎ በመሠዊያው አጠገብ በሰሜን በኩል አኖረው።
በኮረብታም ያሉትን መስገጃዎች አስወገደ፤ ሐውልቶችንም ሰባበረ፤ የማምለኪያ ዐፀዶችንም ነቃቀለ፤ የእስራኤል ልጆች እስከዚህ ዘመን ድረስ ያጥኑለት ነበርና ሙሴ የሠራውን የናሱን እባብ አጠፋ፤ ስሙንም “ነሑስታን” ብሎ ጠራው።
ጉባኤውም ያመጡት የሚቃጠል መሥዋዕት ቍጥር ሰባ ወይፈን፥ መቶም አውራ በጎች፥ ሁለት መቶም የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ ይህ ሁሉ ለእግዚአብሔር የሚቃጠል መሥዋዕት ነበረ።
የሚቃጠለውም መሥዋዕት ከደኅንነቱ መሥዋዕት ስብና ለሚቃጠለውም መሥዋዕት ከሚቀርበው የመጠጥ ቍርባን ጋር ብዙ ነበረ። እንዲሁም የእግዚአብሔር ቤት አገልግሎት ተዘጋጀ።
በሄኖምም ልጅ ሸለቆ ውስጥ ልጆቹን በእሳት አቃጠለ፤ ሞራ ገላጭም ሆነ፤ አስማትም አደረገ። መተተኛም ነበረ፤ መናፍስት ጠሪዎችንና ጠንቋዮችንም ሰበሰበ፤ ያስቈጣውም ዘንድ በእግዚአብሔር ፊት እጅግ ክፉ ነገርን አደረገ።
ሕዝቡን የያዕቆብን ቤት ትቶአልና፤ ምድራቸው እንደ ቀድሞው እንደ ፍልስጥኤማውያን ምድር በሟርት ተሞልቶአልና፤ እንደ ባዕድ ልጆችም ሆነዋልና፤ ብዙ እንግዶች ልጆችም ተወልደውላቸዋልና።
ሕዝቤ በዝሙት መንፈስ ስተዋልና ከአምላካቸውም ርቀው አመንዝረዋልና በትርን ይጠይቃሉ፤ በትሩም ይመልስላቸዋል።