የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።
1 ሳሙኤል 6:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ስለ በደል መባእ ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የሰውነታቸው ምሳሌ የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፦ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱም ለጌት፥ አንዲቱም ለአቃሮን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች አንዱ ስለ አሽዶድ፣ አንዱ ስለ ጋዛ፣ አንዱ ስለ አስቀሎና፣ አንዱ ስለ ጋትና አንዱ ስለ አቃሮን የቀረቡ ናቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለጌታ የላኳቸው የወርቅ ዕባጮች እነዚህ ናቸው፤ አንዱ ስለ አሽዶድ፥ አንዱ ስለ ጋዛ፥ አንዱ ስለ አስቀሎና፥ አንዱ ስለ ጌት፥ አንዱ ስለ ዔቅሮን የቀረቡ ነበሩ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለ በደላቸው የሚከፈሉ ስጦታዎች ይሆኑ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ለእግዚአብሔር የላኩአቸው በእባጮች አምሳል የተሠሩ አምስት የወርቅ እንክብሎች አሽዶድ፥ ጋዛ፥ አስቀሎና፥ ጋትና ዔቅሮን ተብለው በሚጠሩት ከተሞቻቸው ስም የተላኩ ነበሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያን ስለ በደል መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ያቀረቡአቸው የወርቅ እባጮች እነዚህ ናቸው፥ አንዲቱ ለአዛጦን፥ አንዲቱም ለጋዛ፥ አንዲቱም ለአስቀሎና፥ አንዲቱ ለጌት፥ |
የፍልስጥኤማውያን ሴቶች ልጆች ደስ እንዳይላቸው፥ የቈላፋንም ሴቶች ልጆች እልል እንዳይሉ፥ በጌት ውስጥ አታውሩ፤ በአስቀሎናም አደባባይ የምስራች አትበሉ።
እነዚያም አራቱ በጌት ውስጥ ከረዐይት የተወለዱ የራፋይም ወገኖች ነበሩ፤ በዳዊትም እጅ በአገልጋዮቹም እጅ ወደቁ።
አካዝያስም በሰማርያ በሰገነቱ ላይ ሳለ በዐይነ ርግቡ ወድቆ ታመመ፤ እርሱም፥ “ሂዱ፥ ከዚህ ደዌ እድን እንደ ሆነ የአቃሮንን አምላክ ብዔልዜቡልን ጠይቁ” ብሎ መልእክተኞችን ላከ፤ እነርሱም ሊጠይቁለት ሄዱ።
ወጥቶም ከፍልስጥኤማውያን ጋር ተዋጋ፤ የጌትን ቅጥር፥ የኢያቢስንም ቅጥር፥ የአዛጦንንም ቅጥር አፈረሰ፤ በአዛጦንና በፍልስጥኤማውያንም ሀገር ከተሞችን ሠራ።
የተደባለቀውንም ሕዝብ ሁሉ፥ የዖፅ ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፥ የፍልስጥኤም ምድር ነገሥታትንም ሁሉ፤ አስቀሎናንም፥ ጋዛንም፥ አቃሮንንም፥ የአዛጦንንም ቅሬታ፤
“ስለ ሠራው ኀጢአት የበግ መግዣ ገንዘብ በእጁ ባይኖረው ግን፥ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለኀጢአት መሥዋዕት ሁለተኛውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት፥ ለእግዚአብሔር ያቀርባል። ወደ ካህኑም ያመጣቸዋል፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፥ “በኤዶምያስ ይዘጉባቸው ዘንድ የሰሎሞንን ምርኮ ማርከዋልና ስለ ሦስት ወይም ስለ አራት የጋዛ ኀጢአት መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስላቸውም።
የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ወደ ካልኔ ተሻግራችሁ ተመልከቱ፤ ከዚያም ወደ ኤማትራባ እለፉ፤ ከዚያም ወደ ፍልስጥኤም ጌት ውረዱ፤ እነርሱ ከእነዚህ መንግሥታት ይበረታሉ፤ ድንበራቸውም ከድንበራቸው ይሰፋልና።
ይሁዳም ጋዛንና አውራጃዋን፥ አስቀሎናንና አውራጃዋን፥ አቃሮንንና አውራጃዋን፥ አዛጦንንና አውራጃዋን አልወረሳትም።
የእግዚአብሔርም መንፈስ በላዩ ወረደ፤ ወደ አስቀሎናም ወረደ፤ ከዚያም ሠላሳ ሰዎችን ገደለ፤ ልብሳቸውንም ገፍፎ እንቆቅልሹን ለነገሩት ሰዎች ሰጠ። ሶምሶንም ተቈጣ፤ ወደ አባቱም ቤት ተመለሰ።
ፍልስጥኤማውያንም ይዘው ዐይኖቹን አወጡት፤ ወደ ጋዛም አውርደው በእግር ብረት አሰሩት፤ በግዞትም ሆኖ እህል ይፈጭ ነበር።
የእግዚአብሔርንም ታቦት ወደ አስቀሎና ላኩአት። የእግዚአብሔር ታቦት ወደ አስቀሎና በመጣች ጊዜ አስቀሎናውያን፥ “እኛንና ሕዝባችንን ልታስገድሉን የእስራኤልን አምላክ ታቦት ለምን አመጣችሁብን?” ብለው ጮኹ።
ልከውም የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ወደ እነርሱ ሰበሰቡና፥ “በእስራኤል አምላክ ታቦት ምን እናድርግ?” አሉ፤ የጌት ሰዎችም፥ “የእስራኤል አምላክ ታቦት ወደ እኛ ትዙር” ብለው መለሱ። የእስራኤል አምላክ ታቦትም ወደ ጌት ሄደች።
እነርሱም፥ “ስለ መቅሠፍቱ የምንሰጠው የበደል መባእ ምንድን ነው?” አሉ። እነርሱም እንዲህ አሉ፥ “እናንተንና አለቆቻችሁን፥ ሕዝባችሁንም ያገኘች መቅሠፍት አንዲት ናትና እንደ ፍልስጥኤማውያን አለቆች ቍጥር አምስት የወርቅ እባጮች፥ አምስትም የወርቅ አይጦች አቅርቡ።