እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
1 ሳሙኤል 31:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፤ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ ተዋግተውም በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወደቁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፊታቸው ሸሹ፤ ብዙዎቹም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተወግተው ወደቁ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህ ጊዜ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ወጉ፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት፥ በጊልቦዓ ተራራ ላይ የወደቁትን ጥለው ሸሹ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍልስጥኤማውያን በጊልቦዓ ተራራ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሸሹ፤ ብዙዎችም ተገደሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፍልስጥኤማውያንም ከእስራኤል ጋር ተዋጉ፥ የእስራኤልም ሰዎች ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፥ ተወግተውም በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወደቁ። |
እናንተ የጌላቡሄ ተራሮች ሆይ፥ ዝናብና ጠል አይውረድባችሁ፤ ቍርባንንም የሚያበቅል እርሻ አይሁንባችሁ። የኀያላን ጋሻ በዚያ ወድቆአልና፤ የሳኦልም ጋሻ ዘይት አልተቀባምና።
ወሬውን ያመጣለት ጎልማሳም አለ፥ “በጌላቡሄ ተራራ ተዋግተው ወደቁ፤ እነሆም፥ ሳኦል በጦሩ ላይ ተኝቶ ነበር፤ ሰረገሎችና ፈረሰኞችም ተከትለው ደረሱበት።
ለሳኦልም ልጅ ለዮናታን አንድ ሽባ የሆነ ልጅ ነበረው። የሳኦልና የዮናታን ወሬ ከኢይዝራኤል በመጣ ጊዜ የአምስት ዓመት ልጅ ነበረ፤ ሞግዚቱም አዝላው ሸሸች፤ ልትሸሽም ስትሮጥ ወድቆ ሽባ ሆነ። ስሙም ሜምፌቡስቴ ነበረ።
እንዲህም ሆነ፤ በዚያ ወራት ከእስራኤል ጋር ይዋጉ ዘንድ ፍልስጥኤማውያን ጭፍሮቻቸውን ለሰልፍ ሰበሰቡ፤ አንኩስም ዳዊትን፥ “አንተና ሰዎችህ ከእኔ ጋር ወደ ሰልፍ እንድትወጡ በርግጥ ዕወቅ” አለው።
ሳሙኤልም ሳኦልን፥ “ለምን አወክኸኝ? ለምንስ አስነሣኸኝ?” አለው። ሳኦልም መልሶ፥ “ፍልስጥኤማውያን ይወጉኛልና እጅግ ተጨንቄአለሁ፤ እግዚአብሔርም ከእኔ ርቆአል፤ በነቢያት ወይም በሕልም አላሚዎች አልመለሰልኝም፤ ስለዚህም የማደርገውን ታስታውቀኝ ዘንድ ጠራሁህ” አለው።
እግዚአብሔርም እስራኤልን ከአንተ ጋር በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል፤ ነገም አንተና ከአንተ ጋር ያሉ ልጆችህ ትወድቃላችሁ፥ እግዚአብሔርም የእስራኤልን ጭፍራ ደግሞ በፍልስጥኤማውያን እጅ አሳልፎ ይሰጣል።
ፍልስጥኤማውያንም ጭፍሮቻቸውን ሁሉ ወደ አፌቅ ሰበሰቡ፤ እስራኤላውያንም በኢይዝራኤል ባለው ውኃ ምንጭ አጠገብ ሰፈሩ።