ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
1 ሳሙኤል 13:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግሞም እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ በረቱ ሰሙ፤ ሕዝቡም ደንፍተው ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልጌላ ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ፣ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ርኩስ ተቈጥራ ተጠላች” የሚለውን ወሬ ሰሙ፤ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እስራኤላውያን ሁሉ፥ “ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጦር ሰፈር መታ፤ እስራኤልም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የተጠሉ ሆኑ” የሚለውን ወሬ ሰሙ። ሕዝቡም ከሳኦል ጋር ለመሰለፍ ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳኦል ፍልስጥኤማውያንን ድል እንዳደረገ እስራኤላውያን ሰሙ፤ እስራኤላውያንም በፍልስጥኤማውያን ዘንድ የተጠሉ መሆናቸውን ዐወቁ፤ ስለዚህ እስራኤላውያን ሁሉ ከሳኦል ጋር የሚሰለፉ መሆናቸውን ለመግለጥ በጌልገላ ተሰበሰቡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እስራኤልም ሁሉ ሳኦል የፍልስጥኤማውያንን ጭፍራ እንደ መታ፥ ደግሞም እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ዘንድ እንደ ተጸየፉ ሰሙ፥ ሕዝቡም ሳኦልን ለመከተል ወደ ጌልገላ ተሰበሰቡ። |
ያዕቆብም ስምዖንንና ሌዊን እንዲህ አላቸው፥ “ክፉ አደረጋችሁብኝ፤ በዚች ሀገር በሚኖሩ በከነዓናውያንና በፌርዜዎናውያን ሰዎች ዘንድ አስጠላችሁኝ። እኔ በቍጥር ጥቂት ነኝ፤ እነርሱ በእኔ ላይ ይሰበሰቡና ይወጉኛል፤ እኔና ቤቴም እንጠፋለን።”
በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብፅ ሰዎች ርኩስ ነውና በዐረብ በኩል በጌሤም እንድትቀመጡ እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴንነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ እኛም አባቶቻችንም እንስሳ አርቢዎች ነን” በሉት።
የአሞንም ልጆች የዳዊት ወገኖች እንደ አፈሩ ባዩ ጊዜ፥ የአሞን ልጆች ልከው ከቤትሮዖብ ሶርያውያንና ከሱባ ሶርያውያን ሃያ ሺህ እግረኞችን፥ ከአማሌቅ ንጉሥም አንድ ሺህ ሰዎችን፥ ከአስጦብም ዐሥራ ሁለት ሺህ ሰዎችን ቀጠሩ።
እነርሱም፥ “በፈርዖንና በሹሞቹ ፊት ሽታችንን አግምታችሁታልና፥ ይገድለንም ዘንድ ሰይፍን በእጁ ሰጥታችሁታልና እግዚአብሔር ይመልከታችሁ፤ ይፍረድባችሁም” አሉአቸው።
እግዚአብሔርም ኢያሱን፥ “ዛሬ የግብፅን ተግዳሮት ከእናንተ ላይ አስወግጃለሁ” አለው፤ ስለዚህ የዚያ ስፍራ ስም እስከ ዛሬ ድረስ ጌልገላ ተብሎ ተጠራ።
በፊቴም ወደ ጌልገላ ትወርዳለህ፤ እኔም እነሆ፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀርብ ዘንድ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት እሠዋ ዘንድ ወደ አንተ እወርዳለሁ፤ እኔ ወደ አንተ እስክመጣና የምታደርገውን እስከምነግርህ ድረስ ሰባት ቀን ትቈያለህ።”
አንኩስም፥ “በሕዝቡ በእስራኤል ዘንድ እጅግ የተጠላ ሆኖአል፤ ስለዚህም ለዘለዓለም ባሪያ ይሆነኛል” ብሎ ዳዊትን አመነው።