La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ነገሥት 11:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሁለት ጊዜም ከተ​ገ​ለ​ጠ​ለት ከእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቡ​ና​ውን መል​ሶ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሰ​ሎ​ሞን ላይ ቍጣን ተቈጣ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡ ስለ ሸፈተ፣ እግዚአብሔር ተቈጣው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ሰሎሞን ሁለት ጊዜ ከተገለጠለት ከእስራኤል አምላክ ጌታ ልቡ ስለሸፈተ፥ እግዚአብሔር ተቈጣው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሁለት ጊዜ ተገልጦለት ባዕዳን አማልክትን እንዳያመልክ ያዘዘው ቢሆንም እንኳ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር አልታዘዘም፤ ይልቁንም ከእግዚአብሔር እየራቀ ሄደ፤ ስለዚህም እግዚአብሔር በሰሎሞን ላይ ተቈጣ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሁለት ጊዜም ከተገለጠለት፥ ሌሎችንም አማልክት እንዳይከተል ካዘዘው ከእስራኤል አምላክ ከእግዚአብሔር ልቡን አርቆአልና፥ እግዚአብሔርም ያዘዘውን ነገር አልጠበቀምና እግዚአብሔር ሰሎሞንን ተቈጣ።

Ver Capítulo



1 ነገሥት 11:9
20 Referencias Cruzadas  

የል​ቅ​ሶ​ዋም ወራት ሲፈ​ጸም ዳዊት ልኮ ወደ ቤቱ አስ​መ​ጣት፤ ሚስ​ትም ሆነ​ችው፤ ወንድ ልጅም ወለ​ደ​ች​ለት፤ ነገር ግን ዳዊት ያደ​ረ​ገው ነገር ሁሉ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዖዛ ላይ ተቈጣ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በዚ​ያው ቀሠ​ፈው። በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ታቦት አጠ​ገብ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በዚ​ያው ሞተ።


ሰሎ​ሞ​ንም ልዩ ከሆኑ ከአ​ሕ​ዝብ ለአ​ገ​ባ​ቸው ሚስ​ቶቹ ሁሉ እን​ዲህ አደ​ረገ፤ ለጣ​ዖ​ቶ​ቻ​ቸ​ውም መሥ​ዋ​ዕ​ትን ሠዋ፤ ዕጣ​ንም አጠነ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን በሌ​ሊት በሕ​ልም ተገ​ለ​ጠ​ለት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሰሎ​ሞ​ንን፥ “እን​ድ​ሰ​ጥህ የም​ት​ፈ​ል​ገ​ውን ለምን” አለው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ባ​ዖን ለሰ​ሎ​ሞን እንደ ተገ​ለ​ጠ​ለት ዳግ​መኛ ተገ​ለ​ጠ​ለት።


ይህም ነገር በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ክፉ ሆነ፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ላይ መቅ​ሠ​ፍ​ትን አመጣ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም በሙሴ ላይ እጅግ ተቈጣ፤ እን​ዲ​ህም አለ፥ “ሌዋ​ዊው ወን​ድ​ምህ አሮን አለ አይ​ደ​ለ​ምን? እርሱ እን​ደ​ሚ​ና​ገ​ር​ልህ አው​ቃ​ለሁ፤ እነ​ሆም፥ እርሱ ሊገ​ና​ኝህ ይመ​ጣል፤ በአ​የ​ህም ጊዜ በልቡ ደስ ይለ​ዋል።


ልብህን አጥብቀህ ጠብቅ፥ የሕይወት መገኛ ከእርሱ ነውና።


የሕ​ዝቤ ልቡ​ና​ቸው ዝሙ​ትን፥ መጠ​ጥ​ንና ስካ​ርን ወደደ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ በእ​ነ​ርሱ ላይ ወረደ፤ እር​ሱም ሄደ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን በእ​ና​ንተ ምክ​ን​ያት ተቈ​ጣኝ፤ አል​ሰ​ማ​ኝ​ምም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አለኝ፦ ‘ይበ​ቃ​ሃል፤ በዚህ ነገር ደግ​መህ አት​ና​ገ​ረኝ።’


ልጅ​ህን ከእኔ ያር​ቀ​ዋ​ልና፤ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክ​ትም ያመ​ል​ካ​ልና። የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ቍጣ ይነ​ድ​ድ​ባ​ች​ኋል፤ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ች​ኋል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን ሊያ​ጠ​ፋው እጅግ ተቈ​ጣው፤ ስለ አሮ​ንም ደግሞ በዚ​ያን ጊዜ ጸለ​ይሁ።


በኮ​ሬብ ደግሞ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አሳ​ዘ​ና​ች​ሁት፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሊያ​ጠ​ፋ​ችሁ በእ​ና​ንተ ላይ ተቈጣ።


ዴማስ የአሁኑን ዓለም ወዶ ትቶኛልና፤ ወደ ተሰሎንቄም ሄዶአል፤ ቄርቂስም ወደ ገላትያ ቲቶም ወደ ድልማጥያ ሄደዋል።


“ሳኦል እኔን ከመ​ከ​ተል ተመ​ል​ሶ​አ​ልና፥ ትእ​ዛ​ዜ​ንም አል​ፈ​ጸ​መ​ምና ስላ​ነ​ገ​ሥ​ሁት ተጸ​ጸ​ትሁ።” ሳሙ​ኤ​ልም አዘነ። ሌሊ​ቱ​ንም ሁሉ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጮኸ።