1 ቆሮንቶስ 15:50 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞቻችን ሆይ፥ ይህን እንነግራችኋለን፦ ሥጋዊና ደማዊ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርስም፥ የሚፈርሰው የማይፈርሰውን አይወርስም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እነግራችኋለሁ፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ የሚጠፋውም የማይጠፋውን አይወርስም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! የምነግራችሁ ይህ ነው፤ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱም፤ እንዲሁም የሚጠፋው ሟች አካል የማይጠፋውን ሕያው አካል አይወርስም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን፥ ወንድሞች ሆይ፥ ይህን እላለሁ፦ ሥጋና ደም የእግዚአብሔርን መንግሥት ሊወርሱ አይችሉም፥ የሚበሰብሰውም የማይበሰብሰውን አይወርስም። |
በበጎ ምግባር ጸንተው ለሚታገሡ፥ ምስጋናና ክብርን፥ የማይጠፋ ሕይወትንም ለሚሹ እርሱ የዘለዓለም ሕይወትን ይሰጣቸዋል።
እነሆ፥ እርስ በርሳችሁ፥ “እኔ የጳውሎስ ነኝ፤ እኔ የአጵሎስ ነኝ፤ እኔ የኬፋ ነኝ፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ” የምትሉትን እነግራችኋለሁ።
ሌቦች፥ ወይም ቀማኞች፥ ወይም ሰካሮች፥ ወይም ተሳዳቢዎች፥ ወይም ነጣቂዎች፥ የእግዚአብሔርን መንግሥት አይወርሱአትም።
መብል ለሆድ ነው ፤ ሆድም ለመብል ነው፤ እግዚአብሔር ግን ሁለቱንም ይሽራቸዋል፤ ሥጋችሁም ለእግዚአብሔር ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ እግዚአብሔርም ለሥጋችሁ ነው።
ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አያስቱአችሁ፤ ሴሰኞች፥ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ፥ ወይም አመንዝራዎች፥ ወይም ቀላጮች፥ ወይም በወንድ ላይ ዝሙትን የሚሠሩ፥ የሚሠሩባቸውም ቢሆኑ፤
ነገር ግን ወንድሞቻችን እንዲህ ይቀናል፤ የዚህ ዓለም ኑሮ ሁሉ ሊያልፍ ቀርቦአልና፤ አሁንም ያገቡ እንዳላገቡ ይሆናሉ።
በምድር ያለው ማደሪያ ቤታችን ቢፈርስም፥ በሰማይ በእግዚአብሔር ዘንድ የሰው እጅ ያልሠራው ዘለዓለማዊ ቤት እንዳለን እናውቃለን።
እንግዲህ እንዲህ እላለሁ፦ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ይህ ኪዳን ጽኑዕ ነው፤ ከዚህም በኋላ በአራት መቶ ሠላሳ ዓመት ኦሪት መጣች፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሰጠውን ተስፋ ልትከለክል አይደለም።
እንግዲህ በልባቸው ከንቱ አሳብ እንደሚኖሩ እንደ አሕዛብ እንዳትኖሩ ይህን እላለሁ፤ በእግዚአብሔርም እመሰክራለሁ።