ከቤትሳን ጀምሮ እስከ አቤልምሖላና እስከ ዮቅምዓም ማዶ ድረስ በታዕናክና በመጊዶ በጸርታንም አጠገብ በኢይዝራኤል በታች ባለው በቤትሳን ሁሉ የአሒሉድ ልጅ በዓና ነበረ፤
1 ዜና መዋዕል 7:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ፥ በላድና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ ያዕቆብ የተባለ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምናሴም ወሰን ላይ ቤትሳን፣ ታዕናክ፣ መጊዶና ዶር ከነመንደሮቻቸው ነበሩ። በእነዚህም መንደሮች የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤት-ሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የምናሴ ዘሮች ቤትሻንን፥ ታዕናክን፥ መጊዶንና ዶርን እንዲሁም በእነርሱ ዙሪያ የሚገኙትን ታናናሽ ከተሞች በቊጥጥራቸው ሥር አድርገው ነበር። እነዚህ ሁሉ የያዕቆብ ልጅ የዮሴፍ ዘሮች ይኖሩባቸው የነበሩ ስፍራዎች ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምናሴም ልጆች ዳርቻ ቤትሳንና መንደሮችዋ፥ ታዕናክና መንደሮችዋ፥ መጊዶና መንደሮችዋ፥ ዶርና መንደሮችዋ ነበሩ፤ በእነዚህ የእስራኤል ልጅ የዮሴፍ ልጆች ተቀመጡ። |
ከቤትሳን ጀምሮ እስከ አቤልምሖላና እስከ ዮቅምዓም ማዶ ድረስ በታዕናክና በመጊዶ በጸርታንም አጠገብ በኢይዝራኤል በታች ባለው በቤትሳን ሁሉ የአሒሉድ ልጅ በዓና ነበረ፤
ንጉሡም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤትና ቤተ መንግሥቱን፥ ሜሎንንም፥ የኢየሩሳሌምንም ቅጥር፥ አሶርንም፥ መጊዶንም፥ ጋዜርንም ይሠራ ዘንድ ሠራተኞችን መልምሎ ነበር።
በእርሱም ዘመን የግብፅ ንጉሥ ፈርዖን ኒካዑ ከአሦር ንጉሥ ጋር ሊጋጠም ወደ ኤፍራጥስ ወንዝ ወጣ፤ ንጉሡም ኢዮስያስ ከእርሱ ጋር ሊጋጠም ወጣ፤ ፈርዖንም በተገናኘው ጊዜ በመጊዶ ገደለው።
የይሁዳም ንጉሥ አካዝያስ ያን ባየ ጊዜ በአትክልት ቤት መንገድ ሸሸ። ኢዩም፥ “እርሱንም ደግሞ አልተወውም” ብሎ ተከተለው። በይብላሄምም አቅራቢያ ባለችው በጋይ አቀበት በሰረገላው ላይ ወጋው። ወደ መጊዶም ሸሸ፥ በዚያም ሞተ።
ኢዮስያስ ግን ይዋጋው ዘንድ ተጽናና እንጂ ፊቱን ከእርሱ አልመለሰም፤ በእግዚአብሔርም አፍ የተነገረውን የኒካዑን ቃል አልሰማም፤ በመጊዶንም ሸለቆ ይዋጋ ዘንድ መጣ።
ነገሥታት መጡ፤ ተዋጉም፤ በዚያ ጊዜ በመጌዶ ውኆች አጠገብ በቶናሕ የከነዓን ነገሥታት ተዋጉ፤ በቅሚያም ብርን አልወሰዱም።