1 ዜና መዋዕል 27:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእስራኤልም ነገዶች ላይ እነዚህ ነበሩ፦ በሮቤላውያን ላይ የዝክሪ ልጅ ኤልያዛር አለቃ ነበረ፤ በስምዖናውያን ልጅ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ ነበረ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም የየነገዱ የእስራኤል የጦር ሹማምት፤ በሮቤል ነገድ ላይ የተሾመው፣ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር፤ በስምዖን ነገድ ላይ የተሾመው፣ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእስራኤልም ነገዶች ላይ እነዚህ ነበሩ በሮቤላውያን ላይ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር አለቃ ነበረ፤ በስማዖናውያን ላይ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ አለቃ ነበረ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእስራኤል ነገዶች አስተዳዳሪዎች ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ነው፦ የሮቤል ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዚክሪ ልጅ ኤሊዔዘር የስምዖን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የማዕካ ልጅ ሸፋጥያ የሌዊ ነገድ አስተዳዳሪ፦ የቀሙኤል ልጅ ሐሻብያ የአሮን ነገድ አስተዳዳሪ፦ ሳዶቅ የይሁዳ ነገድ አስተዳዳሪ፦ ከንጉሥ ዳዊት ወንድሞች አንዱ የሆነው ኤሊሁ የይሳኮር ነገድ አስተዳዳሪ፦ የሚካኤል ልጅ ዖምሪ የዛብሎን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአብድዩ ልጅ ዩሽማዕያ የንፍታሌም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዝርኤል ልጅ ያሪሞት የኤፍሬም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የዐዛዝያ ልጅ ሆሴዕ የምዕራባዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የፐዳያ ልጅ ኢዮኤል የምሥራቃዊ የምናሴ ነገድ እኩሌታ አስተዳዳሪ፦ የዘካርያስ ልጅ ዩዶ የብንያም ነገድ አስተዳዳሪ፦ የአበኔር ልጅ ያዕሲኤል የዳን ነገድ አስተዳዳሪ፦ የይሮሐም ልጅ ዐዛርኤል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእስራኤልም ነገዶች ላይ እነዚህ ነበሩ፤ በሮቤላውያን ላይ የዝክሪ ልጅ አልዓዛር አለቃ ነበረ፤ በስማዖናውያን ላይ የመዓካ ልጅ ሰፋጥያስ፤ |
በዐሥራ ሁለተኛው ወር ዐሥራ ሁለተኛው አለቃ ከጎቶንያል ወገን የነበረው ነጦፋታዊው ኬልዳይ ነበረ፤ በእርሱም ክፍል ሃያ አራት ሺህ ጭፍራ ነበረ።
ዳዊትም የእስራኤልን አለቆች ሁሉና የፍርድ አለቆችን፥ ንጉሡንም በየተራ የሚጠብቁትን አለቆቹን፥ ሻለቆቹንም፥ የመቶ አለቆቹንም፥ በንጉሡና በልጆቹ ሀብትና ንብረት ላይ፥ መባ ባለበት ላይ የተሾሙትን ጃንደረቦችንም፥ ኀያላኑንና ሰልፈኞቹን ሁሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሰበሰበ።
ከምድያማዊቱም ጋር የተገደለው የእስራኤላዊው ሰው ስም ዘንበሪ ነበረ፤ የአባቱ ቤት አለቃ የስምዖናውያን የሆነ የሰሉ ልጅ ነበረ።